Print this page
Saturday, 23 November 2019 12:19

‹‹ኢትዮጵያዊነት ይለምልም›› የኪነ ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ዘንባባ የማስታወቂያ ድርጅትና በሊማ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ በጋራ የሚያዘጋጁት ‹‹ኢትዮጵያዊነት ይለምልም›› የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት ከነገ በስቲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ዲስኩር፣ ወግ ግጥምና አጭር ተውኔት ለታዳሚው የሚቀርብ ሲሆን ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ኢ/ር ግደይ ዘርዓጽዮን፣ መምህር የሻው ተሰማ (የኮተቤው)፣ ዶ/ር አለማየሁ አረዳ፣ አቶ ፋሲል መርዓዊ፣ አርቲስት አስቴር
በዳኔ፣ ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁንና መንገሻ አሰፋ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል፡፡

Read 10166 times