Print this page
Monday, 25 November 2019 00:00

“ፍትህ ይንገስ ሰላም ይመለስ” የኪነ-ጥበብ ምሽት ህዳር 22 ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

   በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት በየወሩ የሚካሄደው የኪነጥበብ ምሽት ‹‹ፍትህ ይንገስ ሰላም ይመለስ” በሚል ስያሜ የዚህን ወር መሰናዶ በመጪው ሰኞ ህዳር 22 ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይከናወናል፡፡
በምሽቱ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)፣ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትና ዶ/ር መስከረም ለቺሳ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ገጣሚ ነቢይ መኮንን፣ አርቲስት ተፈሪ ዓለሙና ገጣሚ እስጢፋኖስ በፍቃዱ ግጥም የሚያቀርቡ ሲሆን በአርቲስት ፍቃዱ ከበደ ‹‹አሉላ አባነጋ›› የአንድ ሰው ተውኔት ይቀርባል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም አርቲስት ዓለማየሁ ታደሰና ሽመልስ አበራ ወግ እንደሚያቀርቡና  አርቲስት ዳዊት ፍሬው ሀይሉ ትራምፔት እንደሚጫወት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 8241 times