Print this page
Monday, 25 November 2019 00:00

የሲሪላንካው መሪ ታላቅ ወንድማቸውን ጠ/ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

    በቅርቡ ስልጣን የያዙት የሲሪላንካው ፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓካሳ፣ ከትናንት በስቲያ ታላቅ ወንድማቸውን ማሂንዳ ራጃፓካሳን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ራኒል ዊክሬሚሴን ባለፈው ሐሙስ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ፣ ፕሬዚዳንቱ በመዲናዋ ኮሎምቦ በተካሄደ ስነስርዓት፣ የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩትን የ74 አመቱን ታላቅ ወንድማቸውን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቃለ መሃላ አስፈጽመው ወደ ስልጣን ማምጣታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡
በሲሪላንካ ታሪክ ሁለት ዘመዳሞች ከፍተኛ ስልጣን ሲይዙ የአሁኑ የመጀመሪያው እንደሆነ የጠቆመው ዘገባው፤ ፕሬዚዳንቱ ወንድማቸውን መሾማቸው በአንዳንዶች ቢያስተቻቸውም፣ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ስልጣን እዚህ ግባ የማይባል በመሆኑ ሹመቱ እምብዛም እንዳላስደነቃቸው የሚናገሩ መኖራቸውንም አመልክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በፕሬዚዳንትነት የሚያገለግሉት የ70 አመቱ ጎታባያ፣ ታላቅ ወንድማቸው ፕሬዚዳንት በነበሩበት ከ2005 እስከ 2015 በነበሩት አመታት የመከላከያ አማካሪ ሆነው ያገለግሉ እንደነበርና የ185 ሚሊዮን ብር የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፤ ወንድማቸውን በሾሙበት እለት ክሱ እንደተሰረዘላቸውም አክሎ ገልጧል፡፡



Read 3184 times
Administrator

Latest from Administrator