Saturday, 30 November 2019 12:02

ሰሞኑን በምዕራብ ኦሮሚያ አራት ባለሥልጣናት ተገደሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

     በምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ሰሞኑን አራት የመንግሥት ባለሥልጣናት የተገደሉ ሲሆን አካባቢው ለመንግሥት ባለሥልጣናት የስጋት ቀጠና ሆኗል ተብሏል፡፡
ባለፈው እሁድ በምዕራብ ወለጋ አንድ የፖሊስ አዛዥ ሲገደሉ ማክሰኞ ህዳር 15 ደግሞ በምዕራብ ሸዋ ዞን ሁለት ከፍተኛ የዞኑ ባለሥልጣናት መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል::  ከዚያ ቀደም ብለው ባለው ሳምንት በዚያው ምዕራብ ወለጋ የኦሮሚያ መንገዶች ባለሥልጣን አማካሪ መገደላቸውም ይታወሳል፡፡
በምዕራብ ሸዋ ዞን ጎጆ ከተማ የተፈፀመው ግድያ በጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ረጋኔ ከበደና በወረዳው የኦዲፒ ጽ/ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገረመው ላይ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ባለሥልጣናቱ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ከመስሪያ ቤታቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲያመሩ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ከባለሥልጣናቱ ግድያ ጋር በተያያዘ 11 ተጠርጣሪዎች ተይዘው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የኦሮሚያ መንገዶች ባለሥልጣን አማካሪና የምዕራብ ወለጋ ፖሊስ አዛዥ መገደላቸውንም ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ 2012 ዓ.ም ከጀመረ ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራት ውጭም ስድስት ባለሥልጣናት በተመሳሳይ መልኩ መገደላቸውንና ይህም አካባቢውን ወደ ስጋት ቀጠናነት እየቀየረው መሆኑን የአዲስ አድማስ ምንጮች አመልክተዋል፡፡   


Read 9984 times