Print this page
Saturday, 30 November 2019 12:09

የስፖርት ቁማር ቤቶች እንዲዘጉ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(7 votes)

    በአዲስ አበባ ከ65 በላይ ቅርንጫፍ ያላቸው የቁማር ድርጅቶች አሉ

           የእግር ኳስ ጨዋታ የውጤት ውርርድ የሚያካሂዱ የቁማር (Betting) ድርጅቶች እንዲዘጉና ከክልሉ ከተሞች እንዲባረሩ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጠየቀ፡፡ ከውጭ አገራት የመጡ የቁማር ድርጅቶች ተዘግተው ከአገሪቱ እንዲወጡም ማህበሩ ጠይቋል፡፡
ቁማር ድርጅቶች… በህጋዊ ፈቃድ የሚሰሩና ለመንግስት የገንዘብ ምንጭ ቢሆኑም፣ ውድ በሆነው ወጣት ሃይል ላይ የሚያስከትሉትን ቀውስ መመልከት ያስፈልጋል ብሏል፡፡ ማህበሩ ለመንግስት አካላት ባቀረበው አቤቱታ፤ ቁማር ቤቶቹ በክልሉ እየተስፋፉ፣ ወጣቶችን ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየዳረጉ ነው ብሏል፡፡
በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ቁማር ቤቶች የፈጠሩትን ቀውስ በማስረጃነት ጠቅሶ፤ በኡጋንዳ ከባድ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና  ማህበራዊ ቀውስ በማስከተላቸው መታገዳቸውን ጠቁሟል ማህበሩ፡፡ የስፖርት ቁማር ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደሚያስከትል በባለሙያዎች መጠናቱንም ጠቅሷል፡፡ በባህር ዳር ከተማ ተመሳሳይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየተፈጠረ ነው በማለትም ከወዲሁ እርምጃ መወሰድ አለበት ብሏል - ማህበሩ ጠይቋል፡፡

Read 10987 times