ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ‹‹የኢትዮጵያዊነት አምዶች በሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን ግጥሞች›› በተሰኘ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ በብሄራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሂዳል፡፡ ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ጽሑፍ በገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር) የሚቀርብ ሲሆን መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ ታውቋል፡፡ ሚዩዚክ ሜይ ዴይ፣ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ጋብዟል፡፡