Saturday, 07 December 2019 12:06

‹‹የቀትር ጤዛ›› ታሪካዊ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በ25 ዓመቷ ወጣትና የኮምፒዩተር ሳይንስ ምሩቅ ሔቨን ዮሐንስ የተጻፈውና በተዛቡ ትርክቶችና ታሪኮች አገር አሁን ላለችበት ቀውስ ስለመዳረጓ የሚያትተው ‹‹የቀትር ጤዛ›› መጽሐፍ ነገ እሁድ ህዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከ10፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ይመረቃል፡፡
አሁን እየደረሰብን ያለው መፈናቀል፣ ስደት ሞትና ኢኮኖሚያዊ ድቀት በተዛቡና ትክክል ባልሆኑ ታሪኮችና ትርክቶች የሚመጡ ናቸው ይህ የተዛባ ትርክት ካልቆመ ነገ የሚመጣው ክፉ ነገር ከዛሬው ይበልጣል የሚለው ዋናው የመጽሐፉ ማጠንጠኛ ሲሆን ይህን ለማስቆም ከማን ምን ይጠበቃል የሚል የመፍትሄ ሀሳብም ተመላክቶበታል፡፡ በ264 ገጽ ተቀንብቦ በ120 ብር በሚሸጠው በዚህ የመጽሐፍ ምረቃ ላይ የመጽሐፍ ዳሰሳ ስነ ቃል፣ የአዝማሪ ሙዚቃ፣ ውይይትና የጥያቄና መልስ ጊዜ የሚኖር ሲሆን ከታዳሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ደራሲዋ መልስ እንደምትሰጥም ታውቋል፡፡


Read 2057 times