Saturday, 14 December 2019 12:01

ኢዜማ በነገው ምሽት የእራት ፕሮግራም 10 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዷል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

   ስድስት ወራት በፊት ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰብ ፖለቲከኞች ተዋህደው የመሰረቱት ኢዜማ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝበትን የእራት መርሃ ግብር በነገው እለት በኢንተርኮንቲኔንታል የሚያካሂድ ሲሆን ገቢው ፓርቲውን በሃብትና ፋይናንስ ለማጠናከር ይውላል ተብሏል፡፡
አንድ ሰው 2ሺህ ብር ከፍሎ በሚታደምበት በነገ ምሽቱ የእራት መርሃ ግብር ላይ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።
እራት ግብዣው ላይ የሚታደሙ ኢትዮጵያውያን ስለ ኢዜማና አባላቱ እንዲሁም አደረጃጀቱና አወቃቀሩ ግንዛቤ ይሰጣቸዋል በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎችም ይዝናናሉ ተብሏል መድረኩ ለኢትዮጵያ ተመሳሳይ ህልም ያላቸው ወገኖች በአንድነት ተገናኝተው እርስ በእርስ የሚተዋወቁበትና የግንኙነት መስመሮቻቸውን የሚያጠብቁበት ይሆናል ተብሏል፡፡
ኢዜማ በዚህ የገቢና ግብዓት ማሰባሰብ መርሃ ግብሩ ከገንዘብ በተጨማሪ በአይነት ማለትም ህንፃዎች፣ የቢሮ ቁሳቁሶች፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ሀብቶችንም እንደሚያሰባስቡ ተገልጻል፡፡
ለቀጣዩ ምርጫ በሙሉ አቅሙ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጸው ኢዜማ ከ100 በላይ እውቅ ምሁራን የተሳተፈባቸው 18 የፖሊሲ ሰንዶችን ማዘጋጀቱን፣ ከ4 መቶ በላይ የምርጫ ወረዳዎችን አደራጅቶ ማጠናቀቁን፣ በ25 አለም ከተሞች የድጋፍ ማህበር ማቋቋሙንም አስታውቋል።

Read 11008 times