Saturday, 14 December 2019 12:28

14ኛው የኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 14ኛው የኢትዮጵየ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (አርዞፒያ) የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2012 ድረስ በሚቆየው በዚህ ፌስቲቫል ከ50 በላይ የውጭና የአገር ውስጥ ፊልሞች ለእይታ ቀርበው የሚወዳደሩ ሲሆን ከፊልም ፌስቲቫሉ ጐን ለጐን ወጣቱንና ስለ ሰላም የሚሰብክ የፓናል ውይይት ህዝባዊ ገለፃዎች እና የሽልማት ስነስርዓት ይካሄዳሉ፡፡ የፌስቲቫሉን መከፈት አስመልክቶም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በማሪዮት
ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል::

Read 10420 times