Saturday, 21 December 2019 11:58

ኢትዮጵያ በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከዓለም በ16ኛ ደረጃ ተቀምጣለች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

  በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአመራርና በውሳኔ ሰጭነት ደረጃ የሴቶች ተሳትፎ መጠን በእጅጉ የጨመረ ሲሆን በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከአለም በ16ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ፡፡
በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ድርጅትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገ ጉባኤ ላይ እንደተመለከተው፤ ኢትዮጵያ ሴቶችን በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ በኩል ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች፡፡ በ2019 የተባበሩት መንግስታት ባወጣው ሪፖርትም፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በአለም በ16ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧም ተጠቁሟል፡፡  
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀል በመድረኩ ባቀረቡት የዳሰሳ ጥናት ሴቶች በመራጭነት በ19 በመቶ፣ በተመራጭነት በ21 በመቶ ተሳትፏቸው መጨመሩን ገልጸዋል፡፡
ሴቶች በፓርላማ ተመራጭነትና ተሳትፎም ከ25 ዓመት በፊት ከነበረው 3 በመቶ፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 38 በመቶ ማደጉን እንዲሁም በሚኒስትርነት ደረጃም ግማሽ ያህሉን መያዛቸውን አስታውቀዋል - ኮሚሽኑ፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም ሴቶች በከፍተኛ የውሳኔ ሰጭነት ያላቸው ድርሻ ውስን መሆኑንና መሻሻል እንዳለበት በሰሞኑ መድረክ ተመልክቷል፡፡  

Read 11489 times