Saturday, 21 December 2019 12:01

ቴክኖ ሞባይል የተራቀቁ አዳዲስ ብራንድ ሞባይሎች መሸጫ ማዕከሉን ከፈተ

Written by  መታሰቢያ ከሳዬ
Rate this item
(4 votes)

 ቴክኖ ሞባይል የተራቀቁ ዘመናዊ ብራንድ ሞባይሎቹን ለሽያጭ የሚያቀርብበት ማዕከሉን ሰሞኑን መርቆ ከፈተ፡፡
በቦሌ መድሃኒያለም ኤድናሞል አካባቢ የተከፈተው ይኸው የቴክኖ ሞባይል ረቂቅና ዘመናዊ ብራንድ ሞባይሎች መሸጫ ማዕከሉ፣ ኩባንያው በቅርቡ ለኢትዮጵያ ገበያ ያቀረባቸውን ፓንቶም 9 እና ካሞን 12 የተባሉ ሁለት አዳዲስ ብራንዶቹንና ሌሎች ዘመናዊ ሞባይሎቹን ለገበያ የሚያቀርብበት እንደሆነ የኩባንያው ማርኬቲንግ ማናጀር ኤል አሰን መሐመድ ተናግረዋል፡፡
በአዲሱ ማዕከል ውስጥ ለሽያጭ የሚቀርቡት ሞባይሎች በላቀ ቴክኖሎጂና ጥራት የተሰሩና ለአያያዝ አመቺ የሆኑ አዳዲስ ብራንድ ሞባይሎች መሆናቸውን የተናገሩት ሚስተር አሰን፤ ኩባንያው እነዚህን የሽያጭ ማዕከላት ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ በሌሎችም የክልል ከተሞች ለመክፈትና ተደራሽነታቸውን ለማስፋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ሰሞኑን በይፋ በተከፈተው የቴክኖ ዘመናዊ ብራንድ ሞባይሎች መሸጫ ማዕከል ውስጥ ደንበኞች የኩባንያውን ብራንድና ዘመናዊ ሞባይሎች ለማግኘት እንደሚችሉም ሚስተር አሰን በማዕከሉ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተናግረዋል፡፡


Read 2201 times