Saturday, 21 December 2019 12:38

ከ6ሺህ በላይ ሰዎች የተሳተፉበት የሙዚቃ ቪዲዮ ለእይታ ሊቀርብ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ከ1ሺህ 500 በላይ ፈረሰኞችና 5 ሺህ ያህል ሰዎች የተሳተፉበት ‹‹ግባ በለው ሸዋ›› የተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ ለእይታ ሊበቃ ነው።
የሙዚቃ ቪዲዮው በባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት አቶ ተሾመ አየለ (ባለሀገሩ) ፕሮዲዩስ የተደረገ ሲሆን ቀረፃው በደብረ ብርሃን፣ በእምዬ ምኒሊክ የትውልድ ስፍራ ‹‹አንጎለላ›› እና በተለያዩ ቦታዎች መካሄዱን ፕሮዲዩሰሩ ተሾመ አየለ ገልፀዋል።
ሙዚቃው በዋናነት በሸዋ ባህል፣ ታሪክ፣ ስልጣኔ፣ ጀግኖችና በሸዋ አቃፊነት ላይ ተመስርቶ ሸዋን ከነ ሙሉ ክብሩ የሚገልጽ እንደሆነና ብዙ ገንዘብና ድካም የፈሰሰበትም ነው ተብሏል፡፡ ቀረፃው ተጠናቅቆ በኤዲቲንግ ላይ የሚገኘው ይሔው የሙዚቃ ቪዲዮ በቅርቡ ተመርቆ ለእይታ እንደሚቀርብም ታውቋል፡፡


Read 10482 times