Saturday, 21 December 2019 12:49

ለኩላሊት ህሙማን ድጋፍ የሚያደርግ ውሃ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(4 votes)

  ፋብሪካው ጥቅም ላይ የዋሉ ጠርሙሶቹን በግዥ ይሰበስባል
                       
           ከሚያገኘው የሽያጭ ትርፍ ላይ በዓመት 20 ለሚደርሱ የኩላሊት ህሙማንን የሚያሳክምና ለህሙማኑ ነፃ የመጠጥ ውሃ የሚያቀርብ የውሃ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ፡፡
በጎልድ ግሩፕ እየተመረተ ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርበው ‹‹ጎልድ ውሃ›› ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች ሳይገቡበት፣ በዘመናዊ መንገድ በአግባቡ የተጣራ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ሰሞኑን በስካይላይት ሆቴል በተደረገው ፕሮግራም ላይ እንደተገለፀው፤ ፋብሪካው አገልግሎት ላይ የዋሉ የውሃ ጠርሙሶቹን እየሰበሰቡ ለሚያቀርቡ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመክፈት፣ ጠርሙሶቹን እየገዛ ለሌሎች ጥቅሞች ያውላል፡፡ ፋብሪካው ከውሃ ሽያጩ ከሚያገኘው ትርፍ ለኩላሊት ህሙማን እገዛና ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን የተናገሩት የፋብሪካው ሽያጭ ማናጀር አቶ ሲሳይ መንገሻ፤ ይህንን ለማድረግም ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውንና በዓመት 20 ለሚያህሉ ህሙማን ህክምናቸውን እንዲያገኙ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
ፋብሪካው በቡራዩና አምቦ አካባቢ የተገነባ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሥራ የጀመረው የቡራዩ ፋብሪካ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፋብሪካው ለ300 ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል መክፈቱም በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡
ፋብሪካው በ2025 በምሥራቅ አፍሪካ ‹‹ምርጥ 5 ፋብሪካ›› ለመሆን ዕቅድ ይዞ እየተሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

Read 3816 times