Saturday, 28 December 2019 13:00

ሕወሓትንና ህግደፍን ለማስታረቅ እንቅስቃሴ ተጀምሯል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

     ከ20 በላይ አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ወደ አስመራ ይጓዛል
                           
              “ሰለብሪቲ ኢቨንትስ” ለውጡን ተከትሎ የመጣውን የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች እርቅ አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ “እርቂ ዳስ” (የእርቅ - ዳስ) የሚል እንቅስቃሴ መጀመሩን “ሰለ ብሪቲ ኢቨንትስ” አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ምንም እንኳን እርቁ ቢፈጠርም በአሁኑ ወቅት በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሃ.ት) እና በኤርትራው ህዝባዊ ግንባርን ዲሞክራሲን ፍትህን (ህግደፍ) መካከል ባለው ክፍተት ሳቢያ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ሰላም አስተማማኝና ዘላቂ ሊሆን አይችልም፤  በለውጡ ተከፍቶ የነበረው ድንበር መልሶ መዘጋቱም የሁለቱ ፓርቲዎች ውጥረት ያመጣው ነው ብለዋል - የ “ሰብለብሪቲ ኢቨንትስ” ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ገ/ሊባኖስ፡፡
እርቁንና ሰላሙን አስተማማኝ ለማድረግ ሁለቱ ፓርቲዎች እርቅ ማውረድ አለባቸው ያሉት አቶ አብርሃም፤ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ተደጋጋሚ ምክክሮችና ውይይቶች በአገር ውስጥ ሲያከናውኑ ቀጣዩን ውይይት ከህግደፍ ጋር ለማድረግም የድርጅቱ አመራሮች የፊታችን ማክሰኞ ወደ አስመራ እንደሚጓዙ ተናግረዋል፡፡
በቅርቡም ከሃያ በላይ አባላት ያሉት የሀይማኖት አባቶች፣ የጋዜጠኞች፣ የአባ ገዳዎች፣ የአርቲስቶችና የታዋቂ ሰዎች ቡድን ለዚሁ የእርቅ ዳስ ውይይት ወደ አስመራ የሚያመራ ሲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ኡመር እድሪስን ጨምሮ ብዙዎቹ ለጉዞው አዎንታዊ ምላሽ እንደሰጡ ታውቋል፡፡

Read 1913 times