Print this page
Saturday, 28 December 2019 13:59

Infection….በበሽታ መመረዝ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

   በየአመቱ በአለም ላይ 357 ሚሊዮን የሚደርሱ አዲስ በበሽታ መመረዞች infections ይከሰታሉ:: ከእነዚህም ከአራቱ በበሽታ መመረዞች አንዱ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚከሰት ሲሆን የበበሽታ መመረዞቹ (infections) ስማቸውም chlamydia, gonorrhoea, syphilis እና tricho- moniasis በመባል ይታወቃል፡፡ በአማርኛው ቂጥኝ፤ጨብጥ፤ከርክር….ወዘተ ይባሉ የነበሩት ናቸው፡፡
በአለም ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አዲስ በበሽታ መመረዞች infections በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት በየቀኑ ይከሰታሉ፡፡
የስነተዋልዶ አካላት በበሽታ መመረዝ (infection) ሲባል በዚያው በስነተዋልዶ አካል ውስጥ የሚፈጠር ወይንም ከውስጥ አካላት ውጭ በሚያጋጥሙ የተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ ከውጭ የሚያጋ ጥሙ ከሚባሉት ውስጥ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፍ፤ በህክምና አማ ካኝነት ወይንም በሌላ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህም በተፈጥሮ አካል ውስጥ ወይንም በግብረስጋ ግንኙነት ምክ ንያት የሚተላለፍ በሽታ አለዚያም ከሕክምና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ተብሎ የሚገለጽ ሲሆን ሕመሙ በምን ምክንያት እንደተከሰተ እና የመስፋፋቱ ሁኔታ ታይቶም ምክንያቱ ሊታ ወቅ እንደሚችል የአለም የጤና ድርጅት (WHO14 June 2019) ባወጣው መረጃ ገልጾአል፡፡
በየአመቱ በአለማችን ከ340/ሚሊዮን በላይ የሚድኑና አብዛኛቹም የማይድኑ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ በበሽታ መመረዞች (infection) ይከሰታሉ፡፡ በሴቶች ዘንድ ከግብረስጋ ግንኙነት ውጭ የሚከሰቱ በበሽታ መመረዞችም የተለመዱ ናቸው፡፡  
በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉትም ሆኑ ከግብረስጋ ግንኙነት ውጭ የሚተላለፉት በበሽታ መመረዞች (infection) ለእናቶች እንዲሁም በእርግዝና ላይ ላሉ ሴቶች ጤንነት እና ሞት ምክንያት ሲሆኑ ይስተዋ ላል፡፡ ሕመሞቹ በከፋ ሁኔታ የሚያጋጥሙትም በእርግዝና፤ ካለቀኑ ልጅ በሚወለድበት ወቅት፤ እርግዝና ሲጨናገፍ፤ ጽንሱ ህይወቱ በማህጸን ውስጥ ሲጠፋ እና የጽንስ መቋረጥ ሲያጋጥም፤ ጽንስ ተፈጥሮአዊ ችግር ሲገጥመው፤ በመሳሰሉት ምንያቶች እና በማዋለድ ጊዜ ለኢንፌክሽን መጋ ለጥ ሲኖር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት መመረዝ የማህ ጸን ካንሰር ከዚያም ባለፈ ሞት እንዲያ ጋጥም ምክንያት ሊሆን የሚችል ሲሆን ለኤችአይቪ ኤይድስ ቫይረስ መጋለጥም ሌላው በግብረስጋ ግንኙነት ወይንም ግንኙነት ሳይኖርም ሊከሰት የሚችል አደጋ ነው::
የአለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው ይህንን በእናቶች የስነተዋልዶ አካል ላይ ከግብረስጋ ግንኙነት ውጭ የሚፈጠረውን በበሽታ መመረዝ (infection) ለማስወገድ በጤና ተቋማትና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ውጤታማ የሆነ መከላከልና ችግሩ ሲፈጠርም በትክክል አስፈላጊው ሁሉ በተሙዋላበት መንገድ ለማስወገድ የጤና ባለሙያዎች ተግተው ከሰሩ እናቶች ከሚደርስባቸው የአካልና የስነልቡና ጤንነት መጓደል እንዲሁም ከሞት አደጋ ሊተርፉ እንደሚችሉ ገልጾአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህብረተሰቡን ማስተማር እና ቤት ለቤት እያገኙ በበሽታ ስለመመረዝ አስቀድሞ መከላከል ባጠቃላይም ጤናን መጠበቅ የሚቻልባቸውን መንገዶች መጠቆም በህብረተሰቡ መካከል ሊስፋፋ የሚችለውን (infection) በበሽታ መመረዝ በእጅጉ ሊቀንስ ይችላል፡፡
በስነተዋልዶ አካላት ላይ የሚፈጠሩ በበሽታ መመረዞች ከተፈጥሮአዊ አካላት ጋር ተያያዠነት ያላቸው ሲሆን ሴቶችንም ወንዶችንም ሊያጠቁ የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህም በግብረስጋ ግን ኙነት ሳቢያ ከሚተላለፉት በአማርኛ ቂጥኝ… ጨብጥ……ከርክር …ወዘተ እንደሚባሉት ማለት ነው፡፡ በእርግጥ ከግብረስጋ ግንኙነት ውጭ የሚፈጠሩ ሌሎችም አሉ:: ሴቶች በተፈጥሮአቸው በስነተዋልዶ አካሎቻቸው የሚፈጠሩባቸው ኢንፌክሽኖች በብልት አካባቢ ይታያሉ:: ይህ በተፈ ጥሮ ያለ መመረዝ በተለያዩ የህክምና አሰጣጦች ሳቢያ ወደላይኛው ማለትም የማህጸን ክፍል እንዲስፋፋ እና የዘር መተላለፊያ ቱቦን ጭምር ለሕመም የሚያጋልጥበት እድል ሊከሰት ይችላል፡፡ በሰውነት ውስጥ ያልተፈጠረ ከውጭ የሚፈጠር የበሽታ መመረዝ ሕመምም በሕክ ምና ወቅት ተገቢው ቁጥጥር ካልተደረገ ወደ መራቢያ አካል ማለትም ማህጸን ሊስፋፋና አደጋን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በወንዶች በኩል በአብዛኛው በተፈጥሮ ከሚከሰቱት ኢንፌክሽኖች ይልቅ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ ወይም በሕክምና ወቅት የሚያጋጥሙ ኢንፌክሽኖች ይበልጥ ይታያሉ፡፡  
በበሽታ መመረዝ ምክንያት የሚከሰቱት ሕመሞች ከሰውነት ውስጥ በተፈጥሮ የሚከሰቱትም ሆኑ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት ወይም ደካማ በሆነ የሕክምና አሰጣጥ ምክንያት የሚከ ሰቱት ሕመሞች ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ታማሚዎችን እንደሚያሰቃዩ የህክምና ባለሙያዎች ይገል ጻሉ፡፡ ስለዚህም ህክምናው በተመሳሳይ መንገድ የሚሰጥ ነው እንደ የአለም የጤና ድርጅት መረጃ፡፡ በተለይም ሴቶች የደረሰባቸው የመመረዝ ሕመም ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ስለሚያስቸግር ባብዛኛው ለህመማቸው ምክንያት የሆነውን ነገር እነሱው ሲገልጹት መስማት የተለመደ ነው፡፡ ስለዚህም ሕመሙን ከማከም ባለፈ ምክንያቱ ይሔ ነው ብሎ መለየት አስቸጋሪ ነው፡፡
የስነተዋልዶ አካላት ጤንነትን በመጠበቁ ረገድ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማለትም በእርግዝና ጊዜ ክትትል የሚያደርጉበት ወይም የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎት በሚያገኙበት ክሊኒክ ውስጥ ከግብረስጋ ግንኙነት ውጭ የተከሰተ መመረዝ ወይንም ኢንፌክሽን በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ከሚከሰ ተው በበለጠ በታካሚዎች ላይ ይታያል፡፡ የታካሚዎችን መገለል ለማስወገድ በሚያስችል መን ገድ የጤና አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሙያዎች በተገቢውና ጥራቱን በጠበቀ መንገድ የህክ ምናውን ተግባር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል:: ታካሚዎች በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ በሚተ ላለፍ ኢንፌክሽን ምክንያት የታመሙ መሆናቸውን ሌሎች በአካባቢያቸው ያሉ ታካሚ ዎ ችም ይሁኑ ቤተሰብ እንዲያውቁባቸውና ሁለቱም ማለትም ባልና ሚስት የወደፊት ማህበ ራዊ ግንኙነታቸው እንዳይበላሽ የሚሰጉ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
ከ30 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ባክቴሪያ እና ቫይረስ እንዲሁም ፓራሳይትስ ዝርያዎች በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ እንደሚተላለፉ የሚገመት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ስምንት የሚሆኑት በእርግጠ ኝነት በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፉ ተብለው ይለያሉ፡፡ ከስምንቱ ኢንፌክሽኖች አራቱ ማለትም syphilis, gonorrhoea, chlamydia and trichomoniasis የሚባሉት የሚድኑ ሲሆን የቀሩት አራቱ ማለትም ሄፒታይተስ ቢ እና ኤችአይቪ (HIV, and human papilloma- virus) እና herpes simplex virus (HSV or herpes) የተሰኙትን መዳን የማይችሉ በሚል የWHO መረጃ ይለያቸዋል:: በእርግጥ ሕመሞች እስከመጨረሻው ባይድኑም በተለያዩ የህክምና እርዳታ ዎች የሚያደርሱትን ስቃይ መቀነስ ይቻላል፡፡ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ ኢንፌ ክሽኖችን ለመከላከል መሰራት ያለባቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
የባህርይ ለውጥን ለማምጣት የምክር አገልግሎት መስጠት አንዱ የመከላከያ መንገድ ነው፡፡ይህ ዘዴ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፍ በሽታን ለመከላከል እና ኤችአይቪን እንዲሁም ያልተፈለገ እርግዝናን ከመከላከል ጭምር የሚያገለግል ነው::
በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት ስለሚተላለፈው ሕመምና ስለ ኤችአይቪ አስቀድሞ ወይንም ሁኔታዎች ከተፈጠሩም በሁዋላ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተከታታይነት ያለውና ሙሉ የሆነ ትምህርት መስጠት፤
ወሲብን በጥንቃቄ እና እራስን በመከላከል መፈጸም እንደሚገባ እና ኮንዶም መጠቀም አዋጪ መሆኑን የምክር አገልግሎት መስጠት፤
በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት ሕመም ያግጥማቸዋል ተብለው የሚታሰቡ ማለትም በወሲብ ስራ የሚተዳደሩ፤በተመሳሳይ ጾታ ወሲብ ለሚፈጽሙ ፤በመርፌ የሚወሰዱ እጽ የሚወስዱትን በምክር አገልግሎት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ፤
በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት ሕመም የሚተላለፍ መሆኑን እንዲያውቁ የምክር አገልግሎቱ ወይንም ትምህርቱ ለሚያስፈልጋቸው ታዳጊዎች ወይንም ወጣቶች ፕሮግራም በመዘርጋት ማስተማር እና ችግሩን አስቀድሞ መከላከል ያስፈልጋል፡፡  
የምክር አገልግሎቱ ሰዎች የህመሙን ምልክት አስቀድመው እንዲያውቁና የወሲብ ጉዋደኛቸው በህመሙ ከመያዝ አስቀድሞ ሁኔታውን ተናግረው ቅድመ ጥንቃቄ እንዲኖር ለማድረግ አቅም እና እውቀት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ የህብረተሰቡ ንቃተህሊና አለመ ዳበር፤ የጤና ባለሙያዎቹ ስልጠና መጉዋደል በመሳሰሉት ምክንያቶች አለማችን በግብረስጋ ግን ኙነት ሳቢያ የሚከሰትን በሽታ ዛሬም እንደትልቅ ችግር የምትቆጥረውና ብዙ ታማሚዎች የሚ ጎዱበት ነው፡፡    

Read 14720 times