Saturday, 28 December 2019 14:04

“No Country for young men” የስዕል አውደ ርዕይ ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ከአራት ዓመት በፊት የተመሰረተውና ወጣት ሰዓሊያንን በመላው ዓለም ስራቸውንና ተሰጥኦቸውን እንዲያስተዋውቁ የሚያደርገው “አዲስ ፋይን አርት” ጋለሪ የእውቁን ሰዓሊ  ተስፋዬ ኡርጌሳን “No country for young men” የስዕል ኤግዚቢሽን ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ቦሌ መድሃኒያለም ብርሃኔ አደሬ ሞል ጀርባ በሚገኘው ማማስኪችን ያለበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ይከፍታል፡፡
በወረቀትና በሸራ ላይ የተሳሉ ለወጣት ወንዶች አመቺ ያልሆኑ ሁኔታዎችን አጉልተው የሚያሳዩ ከ14 በላይ የሰዓሊው ስራዎች ለእይታ እንደሚቀርቡም አዲስ ፋይን አርት ጋለሪ በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡
የስዕል አውደ ርዕዩ እስከ ፌብራሪ 15 ቀን 2020 ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

Read 927 times