Saturday, 28 December 2019 14:28

የዳንኤል ክብረት በ “ብቻዬን እቆማለሁ” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

   የሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት 33ኛ ስራ የሆነው “ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎችም” መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በዋናነነት ሀ-ለ-ሐ-መ በሚሉ አራት ዋና ዋና ክፍሎችና በስራቸው ባሉ ንዑሳን ርዕሶች ስር በርካታ ወቅታዊ የአገራችንን ሁኔታ የሚዳስሱ ምክሮች፣ ተግሳፆችና አቅጣጫ ጠቋሚ ጉዳዮች ተዳስሰዋል፡፡ “ብቻዬን እቆማለሁ” ለሚለው የመጽሐፉ ማሰናሰኛ በመጽሐፉ ጀርባ ስለ ሴቷ ጀግና አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ እና ስለ ጣሊያኑ የብቻ መቆም ጥያቄ አርበኛዋ የመለሱት መልስ የመጽሐፉ ዋና ማጠንጠኛ ይመስላል፡፡
ዲያቆን ዳንኤል በአጠቃላይ “ስንደማመጥ እናያለን”፣ “ጥይት አንሁን”፣ “ቅድሚያ ፍትህ” እና “ከዴሞክራሲ በፊት ፍትህ እንፈልጋለን” በሚሉት ዋና ዋና ርዕሶች ሥር በርካታ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ዳስሷል፡፡ በ216 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 11476 times Last modified on Saturday, 28 December 2019 14:31