Print this page
Sunday, 05 January 2020 00:00

ኢትዮጵያ ሪድስ የሕጻናት ንባብ ፌስቲቫል አካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ንባብ በኢትዮጵያ እንዲስፋፋና እንዲጎለብት የሚሰራው ‹‹ኢትዮጵያ ሪድስ›› ባለፈው ሳምንት የሕጻናት የንባብ ፌስቲባል ቀን አካሄደ፡፡
ኢትዮጵያ ሪድስ ባለፉት 17 ዓመታት በኢትዮጵያ ቤተ መጻህፍትን በመገንባት የትምህርት መስፋፋትን በመደገፍ፣ በመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ቤተ - መጻሕፍትን በማቋቋም፣ ለቤተ መጻሕፍት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ በመስጠትና መሰል ዋና ዋና ስራዎች የተሰማራ ሲሆን ከነዚህ ተግባራቱ መካከል አንዱ የሆነውን የሕጻናት የንባብ ፌስቲቫል ቀንን ነው ባለፈው ቅዳሜ ከረፋድ 4፡00 እስከ 10፡00 ከአምባ ኤምፓ ጋር በመተባበር ያካሄደው፡፡
በአምባ ኤምፓ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው በዚሁ የሕጻናት ንባብ ፌስቲቫል ቀን፣ በተረት አባት የተረት ትረካ፣ በታዋቂ አርቲስቶችና ደራሲያን የተረት መጽሐፍት ንባብ፣ የተለያዩ የሕጻናትና የቤተሰብ የጫዋታ ውድድሮች፣ የጥያቄና መልስ ውድድሮችና ሌሎችም ዝግጅቶች የተካሄዱ ሲሆን በዚህ መርሃ ግብር መደሰታቸውን በተለይም የሕጻናት ወላጆች ተናግረው ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል፡፡ የሕጻናት የንባብ ፌስቲቫል ቀን በቀጣይነት በተለያዩ ቦታዎች እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሪድስ የአገር ውስጥ ተጠሪ ወ/ሮ የምስራች ግርማ ተናግረዋል፡፡  

Read 8223 times