Sunday, 05 January 2020 00:00

‹‹ገናን ከእኛ ጋር›› የበዓል ፕሮግራም በጄቲቪ ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴመንትና የፕሬስ ስራዎች ድርጅት የተዘጋጀ ‹‹ገናን ከእኛ ጋር›› ልዩ የበዓል ፕሮግራም በገና በዓል ዕለት ታህሳስ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በጂቲቪ ይቀርባል፡፡
በእለቱ ሕጻናት ልዩ የመዝናኛና የመማሪያ መድረክ የሚያገኙ ሲሆን የተረት አባት፣ ትግል፣ የሕጻናት ንባብ ውድድር፣ የአመጋገብ ስነ ሥርዓት፣ ቅልብልቦሽ፣ ሱዚ፣ ሌባና ፖሊስ፣ ገበጣ፣ የኮሜዲ ዝግጅትና በአጠቃላይ ልጆች ባህላቸውን በደንብ እንዲረዱ የሚያደርጉ ጫዋታዎች፣ ተረቶችና ልዩ ልዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ ኮሜዲያን፣ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች፣ ታዋቂ ሰዎች የተረት አባትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዚህ አዝናኝ የበዓል ቀረፃ ላይ እንደተሳተፉም አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡


Read 9290 times