Print this page
Saturday, 11 January 2020 12:07

70ኛው የፊፋ ኮንግረስ ለአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)


                         ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) 70ኛውን ኮንግረስ አዲስ አበባ ላይ በሰኔ ወር መግቢያ ያካሂዳል

          ከአፍሪካ አገራት መካከል ዓለም አቀፉን የእግር ኳስ ጉባዔ በማስተናገድ ኢትዮጵያ ሦስተኛዋ ናት፡፡ ደቡብ አፍሪካ በ2010 እ.ኤ.አ ላይ እንዲሁም ሞሪሽንስ በ2013 እ.ኤ.አ ላይ የፊሄን ኮንግረስ አስተናግደዋል፡፡ እንዲሁም ሞሪስኮ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ አገር ናት፡፡
አዲስ አበባ ለጠቅላላ ጉባዔው አስተናጋጅነት የተመረጠችው ባለፈው 2019 የፈረንጆች ዓመት በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው 69ኛው ኮንግረስ ነው፡፡
የፊፋው ፕሬዚዳንት ጃያኒ አንፋናቲኖ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ አዲስ አበባ የበነበራቸው ቆይታ መነሻነት ነው፡፡ በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ የበርካታ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች መናሐሪያ በመሆኗ ለጉባኤው ተሳታፊዎች መስተንግዶ እንደምትመች አምነውበታል፡፡
በሰኔ ወር መግቢያ ላይ የሚካሄደው 70ኛው የፊፋ ኮንግረስ ለአዲስ አበባ የኮንፍረንስ ቱኒዚያ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር ይሆናል፡፡ ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር 2011 አባል አገራት ልዑካኖች በተጨማሪ የዓለምአቀፍ ሚዲያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አባላት ይሳተፉበታል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎች  ከ1200 በላይ እንደሚሆንም ይገመታል፡፡
ዓለምአቀፉ የእግር ኳስ ማህበር፤ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የአፍሪካ ህብረት ከወራት በፊት አዲስ አበባ ላይ በ3 ዓመት አጀንዳዎች በጋራ ለመስራት ተዘግተዋል፡፡ መዝናን ለመሞገት ለሰላምና ደህንነት፣ ለትምህርት በጋራ ለመስራት ያተኮሩ ናቸው፡፡
በጉባኤው ላይ ለከተማው ውስጥ የሚገኙ ከ10 በላይ ሆቴሎች ለከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ይሆናሉ የፊፋ ዋና ፀሐፊ ፋቲማ ሳማራ እና የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ አህ ከወር በፊት በአዲስ አበባ ልዑካኖች ነበር፡፡
ከኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር እና በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት አካላት ጋር በመገናኘት ውይይት ማድረጋቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡
70ኛው የፊፋ ኮንግረስ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሰብሰቢያ አዳራሽ ለማካሄድ የታቀደ ሲሆን፤ ለአመቺነቱ የዲዛይን ማሻሻያ ይደረግለታል ተብሏል፡፡ ከጠቅላላ ጉባኤው ጋር በተያያዘ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ታዋቂ ኳስ ተጨዋቾች አዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡ በብሔራዊ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ስታዲዬም ላይም የኤግዚቢሽን ግጥሚያ ይኖራቸዋል፡፡
ዓለምአቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ከ1 ዓመት በፊት በፈረንሳይ ፓሪስ ባደረገው ጉባዔ ለ2020 እ.ኤ.አ 810 ሚሊዮን ዶላር በጀት መመደቡን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ በሚካሄደው ጉባዔ ላይ ዋንኛ መነጋገር አጀንዳዎች መካከል ዓለምአቀፉ የእግር ኳስ ማህበር የክለቦች ዓለምዋንጫ በ2021 እ.ኤ.አ በቻይና ለመጀመር ከማሰቡ ጋር ተያይዞ ነው፡፡
የፊፋ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ባለፈው የ2019 ዓመት መጨረሻ ላይ በየ4 ዓመት እንደ ዓለም ዋንጫ የሚካሄደውን የዓለም ክለቦች ዋንጫ ለመጀመር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲና እና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሴፋሬን በዚሁ ጉዳይ ላይ ሙሉ ስምምነት አድርገዋል፡፡ ታላላቅ የዓለም እግር ኳስ ባለሙያዎች እና አሰልጣኞች ውድድሩን እየተቃወሙት ናቸው፡፡
የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር አዲስ አበባ ውስጥ በተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት መሠረት በአፍሪካ ለሚገኙ ት/ቤቶች በሚቀጥሉት 4 ዓመታት 100 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ይደርጋል፡፡


______________________________________________                    1 የገና ጨዋታ


             “…የገና ስፖርት በይበልጥ መዘውተር የጀመረው በተለየ በአፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት እንደነበረ ይነገራል፡፡ በዚሁ ጊዜ ስለተደረገ አንድ የገና ጨዋታ የተገኘው ታሪክ እንደሚለው
“የአፄ ምኒሊክና የእቴጌ ጣይቱ ቡድኖች” በዛሬው ፍልውሃ ሜዳ ላይ ከቀትር በኋላ ተጋጠሙ፡፡ የሁለቱም ቡድን ተወዳዳሪዎች የየግላቸው ባለሟሎችና ጐበዝ ገበሬዎች ነበሩ:: ንጉሱና ንግስቲቱ ቡድናቸውን ሲያበረታቱ ጀንበር ለዓይን ስትይዝ ጨዋታው በእቴጌ ጣይቱ ቡድን አሸናፊነት አለቀ፡፡ አሸናፊው ቡድን ወዲያው ሆታውን ቀጠለ፡፡
“እጅ የለውም ወይ እጅ የለውም ወይ፤ የሚኒሊክ ቡድን ሩር አይለጋም ወይ” “ብርሌው ብድግ ጠጅ ዶቅዶቃ የሚኒሊክ ቡድን ፍልውና ተወቃ” ብለው በማበሳጨት በዕለቱ ተለያዩ:: የሚኒሊክ ቡድንም በመሸነፉ አዝኖ ለሊቱን በመምከር ዕቅድና ስልት ሲያዘጋጅ አድሮ በማግስቱ በዚያ ሜዳ ላይ ጨዋታው እንዲደረግ አሳሰበ፡፡
በማግስቱ ግማሽ ቀን የወሰደ ውድድር ተደርጐ የአፄ ሚኒሊክ ቡድን ረታ፡፡ የሚኒሊክ ቡድንም በፋንታው “አራሽ ባየሽ የኛ ጣይቱ አፍሽ በዳበሽ” አሏቸው ይባላል፡ በዛው ዘመን በቀድሞ የገና ጨዋታ ጊዜ መኳንንቱ በሌንደን ጐራዴ ጥንግ ይለጉና ይጫወቱ እንደነበረ በታሪክ የሰፈረ ሲሆን በጨዋታውም ሎሌና ጌታ ሳይቀር ይሳተፉ እንደነበረና በሚደርሰውም አደጋ ቂም መያያዝ ስላልነበረ፤ “በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፤ በገና ጨዋታ አየቆጡም ጌታ” ተብሎ እንደሚዘፈን የዛው ዘመን ማረጋገጫዎች ያስረዳሉ፡፡

             2. የግብግብ /ትግል/ ስፖርት

    ግብግብ ከዚያ መጣ፤ ከዚህ ተገኘ፤ መቼ ተጀመረ? የሚል የተጨበጠ መረጃ ባይኖርም የጥንት ኢትዮጵያዊያን የጉልበታቸው ጥንካሬ የሚለካው በታጋይነታቸው እና በግብግብ ከፍተኛ ዝናን ያገኙ እንደነበር የሚያወሳው በ1992 የታተመውን ትንሽ የህግና ደንብ መጻሐፍ ነው፡፡
“እንደዛሬው በብሔራዊ ደረጃ ሻምፒዮናነት ባይኖርም በመንደራቸው በአካባቢያቸው ታጋዮች ይመለመላሉ:: በተመሳሳይ እድሜ ይመደባሉ ከዚያም የአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ በተሰበሰበበት ከፍተኛ የግብግብ ውድድር በየቦታው እንደሚደረግ የቀድሞ አባቶች ይመሰክራሉ፡፡ የአንድ አካባቢ ወይም የአንድ መንደር አሸናፊ
የሆነ ታጋይ ከሌላው አካባቢ ታጋይ በአውደ ዓመት ቀን እንዲታገሉ ይደረጋል አሸናፊ የሆነው ከአካባቢው የጐበዝ አለቃ ሽልማት ይሰጠዋል::

           3. የሱሉስ ገበጣ

    ገበጣው ከእንጨት ወይም ከድንጋይ ሊሰራ ይችላል፡፡ የገበጣው ቁመት ከ50 ሴ.ሜ ያልበለጠ፤ ጐኑ (ወርዱ) ከ30 ሴ.ሜ ያልበለጠ መሆን አለበት፣ እያንዳንዱ ጉድጓድ ጥልቀቱ ወደ ውስጥ 2 ሴ.ሜ ይሆናል፡፡
ከእያንዳንዱ ጉድጓድ መካከል ሊኖር የሚገባው ርቀት 2 ሴሜ ሲሆን አሠራሩም 6.6.6 ጉድጓዶች በተርታ መደዳውን ይኖሩታል፤ የጉድጓዱ ዲያሜትር ወደ ጐን 6 ሴ.ሜ ሆኖ ክብ መሆን አለበት፡፡ በዚህ አይነት የተሰራው ባለ 18 ጉድጓዶችና 2 ጠጠር ማስቀመጫ ጉድጓዶችን ዲያሜትራቸው 12.12 ሴ.ሜትር ሲሆን ወደ ውስጥ ጥልቀታቸው 2 ሴ.ሜ ይሆናል፡፡ የጠጠር መቀነሻ 2ቱ ጉድጓዶች በገበጣ ቁመት በኩል ከመካከል ላይ አብረው የተቀረፁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ መጫወቻ ጠጠሮቹ ከጉድጓዶች ውስጥ ለማፈስና እያንጠባጠቡ ለመሄድ ምቹ ናቸው፡፡ የወንዝ ጠጠር መጠኑ ብይ የሚያክል፤ የብይ ጠጠር፣ የዛፍ ፍሬ ድብልብል መጫወቻ ሊሆኑ ይችላል፡፡ ጠጠሮቹ ከማንኛውም ብረት የተሰሩ ይሆናሉ፡፡


              4. የፈረስ ሽርጥ
የግልቢያ ሜዳ  መጠን ቁመቱ  ከ400-600 ሜትር  ጐኑ ከ30-50 ሜትር  ያለው ሆኖ መሬቱ ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡
በነጭ ኖራ በ10ሣ.ሜ ስፋት መቀባት አለበት::


                         5. ኮርቦ (ጌንጉ/ኮረሽ)

          ኮርቦ የተባለው ስፖርታዊ ጨዋታ በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ይታወቃል፡፡ በቤኒሻንጉል ከጥንት ጀምሮ አባቶችና እናቶች ሲጫወቱት ኖረዋል፡፡ ደብዛው ያልጠፋ ወንድና ሴት የማይለይ በማነጣጠር ላይ የተመሰረተ ከነባር ስፖርቶቻችን ተደናቂነትን የያዘ የባህል ስፖርት ነው፡፡
የኮርቦ ጨዋታ አመጣጡ የጥንት ሰዎች በወጣትነታቸው ወደ አደን ከመሰማራታቸው አስቀድመው ከሚያደርጉት ከፍተኛ ልምምድ ጋር ይያያዛል፡፡ የአደን ልምምዱም ለጥቂት ቀናት ሳይሆን ለጅም ዓመታት የሚቀጥል ነው:: ማንኛውም ሰው ለአደን ብቁ ነው ተብሎ እስኪነገርለት ድረስ ያለ ችግር የክንዱ ጥንካሬ፤ የውርዋሮው ርቀት፤ የአቅጣጫ (የኢላማ) አነጣጠሩ፤ የሰውነቱ ቅልጥፍና፣ በአጠቃላይ ለአደን ብቁ የሚሆንበት ከፍተኛ ልምድ የሚገኝበት ስፖርት ነው፡፡
ኮርቦ ክብ ሆኖ በማይሰባበር መጠምዘዝ ከሚችል ከጠንካራ ሐረግ ወይም ሸምበቆ በመሬት ላይ መሽከርከር የሚችል ሆኖ የተሰራ ነው፡፡ አጨዋወቱም በሁለት ዓይነት የተመደበ ነው፡፡


                    6 የፈረስ ጉግስ ጨዋታ

            የፈረስ ጉግስ ስፖርት ታሪክና አመጣጥ በፈረስ ሽቅድምድም (ሽርጥ) ስፖርት ታሪክ እንደተገለጠው ሆኖ ለፈረስ ሽቀድምድም የተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ከፍተኛ ልምምድ ለጉግሱ ብቁ በመሆን ነው፡፡
ይህም ማለት መጀመሪያ ምን ያህል በሌጣ ፈረስ፣ በተለጐመ ፈረስ፣ ኮርቻ በተጫነ ፈረስ በየደረጃው በየጊዜው የፈረስ ግልቢያ መቻሉን ያጠናል፡፡ ምንም ነገር ከአለንጋ በስተቀር ሳይዝ እየጋለበ ከፈረሱ ጀርባ እየተንሸራተተ ወደ ጉያው እየወረደ ከዚያም እጋማው ላይ እየተቀመጠ ከፍተኛ የግልቢያ ችሎታውን ካስመሰከረ በኋላ ለጉግሰኛነት ይታጫል ወይም ይመረጣል፡፡
በቀድሞ የጉግስና የፈረስ ስፖርት ታሪክ በፈረሰኛነታቸው የታወቁና የተመሰረከላቸው ጀግኖችን መሪዎች የፈረስ ስም እየተባለ ከመጠሪያ ስማቸው ሌላ ይሰየምላቸው እንደነበረ ታሪክ ይናገራል ለምሳሌ
“አፄ ቴዎድሮስ - አባ ታጠቅ
አፄ ምኒልክ - አባ ዳኘው
አፄ ዮሐንስ - አባ በዝብዝ” ወዘተ
ጉግስ በከፍተኛ ደረጃ የሚታወቀውና የሚዘወተረው በበዓላት ሰሞን ነው፡፡ በአሁኑም ወቅት ይህ ስፖርት ጨርሶ ደብዛው ያልጠፋ በአንዳንድ በዓላት ጊዜ የሚጫወቱትና የሚያፈቅሩት ስፖርት ለመሆኑ የምዝገባውና የጥናቱ መረጃ ያመለክታል፡፡
በፈረስ እየጋለቡ ኮርባ መቆም፡፡ በእግር እየሮጡ (ቆሞ) በዘንጉ ማቆም ወደ አየር የተወረወረውን ኮርቦ በዘንጉ ማሹለክ ናቸው:: አጨዋወቱም በሁለት ቡድን በመሆን ይከናወናል፡፡


            ይህ ጽሑፍ የተቀነጨበው በ1992 ዓ.ም በኢትዮጵያ ባህላዊ ስፖርት ፌዴሬሽን ተሻሽለው የቀረቡ ባህላዊ ስፖርቶች ደንብና ህጐች የሚል ርዕስ ይዞ ከታተመው ትንሽ መጽሐፍ አጭር መግቢያ ላይ ነው፡፡ ይኸው መጽሐፍ በገጽ 6 ባሰፈረው መግቢያ “…ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች” ባህላዊ ስፖርቶች ተመሳሳይነት ያላቸውንና በሁሉም ክልል የታወቁና ይዘወተሩ የነበሩትን ባህላዊ ስፖርቶች በቅድሚያ ተመርጠዋል፡፡ ታሪካቸውን ሳይለቁ በአዲስ ስርዓትና ህግ ጐጂ ክፍላቸውን በማስቀረት ጠቃሚዎቹን፣ ሊያድጉና ሊስፋፉ የሚችሉትን በመለየት ነው፡፡ ለጊዜው ለስድስቱ ባህላዊ ስፖርቶቻችን በተሻለ መልኩ ህግ ተቀርፆላቸዋል” ሲል ያትታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ235 በላይ ባህላዊ ስፖርቶች ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ የህበረተሰብ ክፍሎች ይደረጋሉ፡፡ የኢትዮጵያ ባህላዊ ስፖርት ፌዴሬሽን ከእነዚህ ባህላዊ ስፖርቶች ውስጥ በተለይ 10 በመምረጥ ሰርቶ ነበር፡፡ አስፈላጊውን ጥናትና ምርምር በማድረግ በተሻሻለ መስኩ ህግ ተቀርፆላቸው ሊስፋፉና በውድድር በርካታ ህብረተሰብን እያሳተፉ እንዲያድጉ የሚያስችል ስርዓት ዘርግቶ ሊንቀሳቀስም ሞክሯል፡፡ ይሁንና ጥረቶቹ ውጤታማ አይደለም፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት የባህል ስፖርቶች ተስፋፍተው ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ ሊኖርባቸውም ያ ግን አልሆነም፡፡
የኢትዮጵያ ባህላዊ ስፖርት ፌዴሬሽን የቴክኒክ ኮሚቴ፤ ከተለያዩ ባለሙያዎች፣ ከክልል መስተዳድሮች ከምሁራኖች ጋርና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መስራቱ ለስፖርቶች ለውጥ ዕድገት አመቺ ለሆነ ነበር፡፡ በአንፃሩ ግን ስፖርቶቹ እየጠፋ መጥተዋል፡፡ በመተባበር በኢትዮጵያ በጣም ከሚዘወተሩ 10 ባህላዊ ስፖርቶች መካከል ለ6ቱ የባህል ስፖርቶች ደንብና ህግ በመቅረጽ በዚሁ በ1992 ዓ.ም በግንቦት ወር ባወጣው አነስተኛ ዕትሙን የኢትዮጵያ ባህላዊ ስፖርት ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል፡፡ እነዚህ 6 ባህላዊ ስፖርቶች የገና ጨዋታ፣ የግብግብ ጨዋታ፣ የሱሉስ ገበጣ ጨዋታ፣ የባለ 12 ጉድጓድ ገበጣ ጨዋታ፣ የፈረስ ሽቅድምድም (ሽርጥ) ጨዋታ፣ የፈረስ ጉግስ ጨዋታና የኮርቦ ጨዋታ ናቸው፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ጽሑፍ ከላይ ከጠቀስነው መጽሐፍ የተወሰደ ሲሆን ስለእነዚህ 6 ባህላዊ ስፖርቶች ታሪካዊ አመጣጥና ሌሎች ጉዳዮችን ባጭሩ ያስተዋውቃል፡፡

Read 1996 times