Print this page
Saturday, 18 January 2020 12:51

“ኦፌኮ” እና “ኢዜማ” ህዝባዊ ስብሰባዎችን እያካሄዱ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

  አክቲቪስት ጀዋር መሐመድን በአባልነት ያካተተውና በፕ/ር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በሀረር፣ ድሬ ደዋ፣ ጭሮ ከተሞች የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ ማድረጉን ያስታወቀ ሲሆን ኢዜማ በበኩሉ፤ በሐዋሣ ከተማ ህዝባዊ ውይይት አድርጓል፡፡
ኦፌኮ በሶስቱ ከተሞች ባደረጋቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች፤ ስለ ፓርቲው አላማና ፕሮግራም ማብራሪያ መሰጠቱን እንዲሁም በቀጣዩ ምርጫ ደጋፊዎቻቸው በጊዜ ምዝገባ አከናውነው የምርጫውን ቀን እንዲጠባበቁ ምክክር መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በፕ/ር መረራ ጉዲና፣ በምክትላቸው አቶ በቀለ ገርባና በፓርቲው አዲስ አባል ጀዋር መሐመድ የተመራው የልዑክ ቡድን፤ በሀረር፣ ጭሮ ከተሞች የፓርቲውን ጽ/ቤቶች መርቆ ስራ ማስጀመሩም ታውቋል፡፡
አፌኮ በዛሬው እለትም በሠላሌ ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግ አዲስ አድማስ ከፓርቲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በቀጣይም በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች በስፋት ህዝባዊ ስብሰባዎችን ለማድረግ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡
ኢዜማ በበኩሉ፤ በመሪው ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የተመራ ህዝባዊ ስብሰባ በሃዋሣ ከደጋፊዎቹና አባላቱ ጋር ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ፓርቲው ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማም ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ እቅድ ይዟል፡፡

Read 11955 times