Saturday, 18 January 2020 13:22

የአፄ ቴዎድሮስ 201ኛ የልደት መታሰቢያ በአል በጎንደር በድምቀት ተከበረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

  የአፄ ቴዎድሮስ 201ኛ የልደት መታሰቢያ በአል ሐሙስ ጥር 7 ቀን 2012 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በቴዎድሮስ አደባባይ በድምቀት ተከበረ፡፡ በእለቱ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች የከተማው ማህበረሰብ ለጥምቀት በዓል ከተለያየ ቦታ የተሰባሰቡ እንግዶችና ከያኒያን በተገኙበት ነው የመታሰቢያ በአሉ የተከበረው፡፡
በእለቱ የአፄ ቴዎድሮስን ሕይወትና ሥራ የሚዘክሩ ፎቶግራፎች ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ የከበሩ ማዕድናት፣ የምግብና መጠጥ ቅመሱልኝ ኤግዚቢሽን ለእይታ የቀረበ ሲሆን የአዝማሪ ማርች ባንድ አፄ ቴዎድሮስና ባለሟሎቻቸውን፣ ገብርዬንና ልጅ አለማየሁ ቴዎድሮስን ጨምሮ አፄ ቴዎድሮስን የሚዘክር ምስለ ተውኔት፣ ፉከራና ሽለላ፣ በሀውልቱ ሥር ሻማ የማብራት፣ የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥና የመድፍ መተኮስ ሥነ ሥርዓት መካሄዱን የገለፁት የጎንደር የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረ ማሪያም ይርጋ፣ ይህ የልደት መታሰቢያ በዓል የጥምቀትን በዓል ከሚያደምቁ የተለያዩ ዝግጅቶች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፎቶ የማዕድናት፣ የምግብና የመጠጥ ኤግዚቢሽኑም እስከ ዛሬ ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

Read 10758 times