Saturday, 25 January 2020 11:46

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በአዋጅ እንዲቋቋም ሚኒስትሮች ም/ቤት ወሰነ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(6 votes)

 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮችና ጠቅላይ ም/ቤት በአዋጅ ተቋቁሞ፣ ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረው የሚያስችለው አዋጅ፤ በሚኒስትሮች ም/ቤት ፀድቆ ወደ ፓርላማው ተልኳል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረው ከ60 አመታት በላይ ለመንግስት ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረ ጉዳይ መሆኑን ለሚኒስትሮች ም/ቤት በቀረበው ጥያቄ ላይ ተመልክቷል፡፡
ም/ቤቱ እስከ ዛሬ እንደ ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት  ተመዝግቦ የሚገኝ የነበረ ሲሆን የሚኒስትሮች ም/ቤት ውሣኔ፣ ይህን ሽሮ መጅሊሱ ራሱን ችሎ በአዋጅ የተቋቋመ ተቋም እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል - የህግ ባለሙያዎች
ም/ቤቱ ራሱን በቻለ አዋጅ የተቋቋመ ሲሆን፤ በቀጣይ ከሌሎች ሃይማኖቶች የሚነሱ ጥያቄዎችን አንድ ላይ ለማስተናገድ ግን ተጨማሪ ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔው ለፓርላማ ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

Read 14811 times