Saturday, 25 January 2020 12:23

የ2 ሺህ 153 ቢሊየነሮች ሃብት ከ60 በመቶ የአለም ህዝብ አጠቃላይ ሃብት ይበልጣል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

    325 ሚ. የአፍሪካ ሴቶች ያፈሩት ገንዘብ ቢደመር፣ 22 ባለጸጎች ከያዙት ገንዘብ አይደርስም

             በአለማችን የሃብት ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ እየሰፋ መምጣቱንና የአለማችን 2 ሺህ 153 ቢሊየነሮች ያፈሩት ሃብት፣ 60 ከመቶ በላይ የሚሆነው የአለም ህዝብ ወይም 4.6 ቢሊዮን ሰዎች ካፈሩት አጠቃላይ ሃብት የሚበልጥ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ኦከስፋም ኢንተርናሽናል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ይፋ ያደረገው አለማቀፍ ሪፖርት እንደሚለው፤ የአለማችን ቢሊየነሮች ቁጥር ባለፉት አስር አመታት በእጥፍ ያደገ ሲሆን፣ ድሆች በተለይ ደግሞ ሴቶች ሃብታቸው እየተመናመነ የከፋ ኑሮን በመግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡
በአህጉረ አፍሪካ የሚገኙት 325 ሚሊዮን ያህል ሴቶች በሙሉ ያፈሩት ገንዘብ ቢደመር፣ ሃያ ሁለቱ የአለማችን ግንባር ቀደም ባለጸጎች ካላቸው ገንዘብ በእጅጉ እንደሚያንስ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ሃብት በተወሰኑ ዜጎች እጅ እየተሰበሰበ ሰፊው ህዝብ ግን ቁልቁል ወደ ድህነት በመዝቀጥ ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል::
መንግስታት በድሆችና በባለጸጎች መካከል ያለውን ሰፊ የሃብት ልዩነት ለማጥበብ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን አውጥተው መተግበር እንዳለባቸው የሚገልጸው ሪፖርቱ፤ የሃብት ልዩነቶችን በተጨባጭ ለማጥበብ በቢሊየነሮች ላይ የሚጥሉትን ግብር በመጪዎቹ አስር አመታት በ0.5 መጨመር እንዳለባቸውም ይመክራል፡፡



Read 1496 times