Saturday, 25 January 2020 12:40

‹‹ተባብሮ የመኖርና የመስራት ጥበብ›› መጽሐፍ ረቡዕ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    በደራሲ ሙላቱ በላይነህ (ዶ/ር) የተጻፈውና ተባብሮ በመኖርና በመስራት ፋይዳዎች ላይ የሚያጠነጥነው ‹‹ተባብሮ የመኖርና የመስራት ባህል›› መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል እንደሚመረቅ የዝግጅቱ አስተባባሪ ሰምና ወርቅ ኢንተርቴይንመት አስታወቀ፡፡
በዕለቱም በመጽሐፉ ይዘትና ተባብሮ በመኖርና በመስራት ፋይዳና እሳቤ ዙሪያ የፍልስፍና መምህሩ ዮናስ ዘውዴ፣ ደራሲው ሙላቱ በላይነህ (ዶ/ር)፣ አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ አቶ ማርቆስ ታደሰ፣ እንዲሁም ገጣሚያኑ በቃሉ ሙሉ፣ ኤሊያስ ሽታሁንና መዓዛ ብርሃኔ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡና መድረኩ በአርቲስት ደበሽ ተመስገን እንደሚመራ ታውቋል፡፡  

Read 1125 times