Print this page
Saturday, 25 January 2020 12:57

‹‹መንገደኛው ባለቅኔ ከድርሰተቴ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   ከቡና አምራች ከበርቴ ቤተሰብ እንደተገኘና በደርግ ዘመነ መንግሥት ቅኔና ትንቢት መሳይ ጉዳዮችን በመናገር የብዙዎችን ቀልብ ይስብ ስለነበረው ከድርሰተቴ ሕይወትና ኑረት የሚተርከውና በተስፋዬ አየለ የተጻፈው ‹‹መንገደኛው ባለቅኔ ከድርሰተቴ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ።
መጽሐፉ በዋናነት በባለቅኔው ከድርሰተቴ ፍልስፍናዎች፣ ሀቂቃ ትንቢቶች፣ ዘመን ተሻጋሪ እውነታዎችና የሀቅ ኑረት ተጋድሎዎች፣ በምናብ ተቃኝተው የቀረቡበት የቅኔ መድበል እንደሆነ ፀሐፊው በመግቢያው አስፍሯል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በመጽሐፉ ጀርባ ባሰፈሩት ማስታወሻ ከድርሰተቴ ለሀቅ መኖርን ያስተማረኝ ስለሀቅ የኖረ ተራማጅ ነው ክፉ ዘመን ሀቅን እንዳልናገር አንደበቴን በለጎመኝ ጊዜ አፍ የሆነኝ ባለውለታዬም ነው፡። ‹‹ሳተቴ በሚል ርዕስ ‹‹ዲርአዝ›› በሚል የብዕር ስም ስለሀቅ ተጋድሎዎቹ፣ ረቂቅ ፍልስፍናዎቹና ትንቢቶቹ በመጻፍ ሀቅን መተንፈሻ ሆኖኛል…›› ብለዋል፡፡
ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮም ስለከድርሰተቴ ባለቅኔ ብቻ አይደለም ከዚያም ከፍ ይላል እኛ ግጥሞቹን ንፋስ ላይ የጽፋቸዋል…›› እያለ ይቀጥላል፡፡ በ269 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ፣ በ121 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም ‹‹የንጋት ሽክሹክታዎች›› የግጥም መድበል፣ ‹‹ሽንቁርና ውታፍ›› የከድርሰተቴ ታሪክ የተካተተበት የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ፣ ‹‹ODAAJALA›› የኦሮሞኛ አጫጭር ልቦለድ ስብስብ ለንባብ ያበቁ ሲሆን በቀጣይ ‹‹ድንቃር›› ወጥ ልብ ወለድና ‹‹የወለሎታት ስብስብ›› በኦሮምኛ ቋንቋ ለማስነበብ ዝግጅት አጠናቅቀዋል፡፡

Read 22944 times