Saturday, 08 February 2020 15:04

የከያኒ ጌትነት እንየው ‹‹ውበትን ፍለጋ›› መጽሐፍ ምረቃና የምስጋና ፕሮግራም የካቲት 16 ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  ማክሰኞ ሊካሄድ የነበረው የእውቁ ከያኒ ጌትነት እንየው ‹‹ውበትን ፍለጋ›› መጽሐፍ ምረቃና የምስጋና ፕሮግራም የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በምረቃና በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትርና ኪነ ጥበባት ትምህርት ክፍል መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ወርቁ፣ አርቲስቶቹ ደበበ እሸቱ፣ አበበ ባልቻ፣ ዓለማየሁ ታደሰ እንዲሁም ገጣሚያኑ ኤፍሬም ስዩም፣ ሰለሞን ሳህለ፣ ትዕግስት ማሞና ምልዕቲ ኪሮስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
በዕለቱ ከያኒው ለረጅም አመታት ላበረከተው የኪነ ጥበብ አበርክቶ ምስጋና የሚቀርብለት ሲሆን እውቁን ተውኔቱን ‹‹ውበትን ፍለጋ››ን ጨምሮ በርካታ ሰራዎቹን የያዘው ‹‹ውበትን ፍለጋ›› መጽሐፉ የሚመረቅ ሲሆን፣ ዘጋቢ ፊልም፣ ቅንጭብ ተውኔትና ሙዚቃም ለታዳሚ እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡
የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው ይሄው መርሃ ግብር በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ምክንያት ለየካቲት 16 መዛወሩን የዝግጅቱ አስተባባሪ ሰምና ወርቅ ኢንተርቴይንመንት አስታውቋል፡፡

Read 11699 times