Print this page
Saturday, 15 February 2020 12:21

‹‹ጎቲም ሲሞን›› በአዲስ መልክ ታትሞ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

  የሞገደኛው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ‹‹ጎቲም ሲሞን›› መጽሐፍ በአዲስ መልክ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ የምስራቅ አፍሪካን ምስቅልቅል ፖለቲካና የአገራችንን የውጭም ሆነ የውስጥ ፖሊሲዎች በጥልቅ በመተንተን የሚታወቀው ጋዜጠኛው በ‹‹ጎቲም ሲሞን›› የመጀመሪያ እትሙ ያልተካተቱና መካተት የሚኖርባቸውን የመሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ፣ የቀንዱን አካባቢ ውጥንቅጥ የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ በአጠቃላይ አሁን ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ አካትቶና አዳብሮ በድጋሚ ለንባብ አብቅቶታል። በ40 ዋና ዋና ክፍሎች ተከፋፍሎ በ257 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ130 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በሁሉም መጽሐፍት መደብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በፋና ሬዲዮ፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በቅርቡ በተዘጋው ኢኤንኤን ቴሌቪዥን ሲሰራ የቆዬ ሲሆን በናሁ ቲቪ ያዘጋጅ በነበረውና የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ በሚተነትንበት ‹‹ናሁ ፕረስ›› ይበልጥ የሚታወቅ ሲሆን በአሁን ሰዓት በትግራ ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ‹‹ኢትዮ ፎረም›› ፕሮግራም በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

Read 11644 times