Saturday, 15 February 2020 12:26

ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው

Written by  ሰላም ገረመው
Rate this item
(1 Vote)

   ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የቴዲ በቀጣይ ቅዳሜ የሙዚቃ ኮንሰርት የሚካሄድ መሆኑ ተገለፀ:: ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከላዮን ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የተዘጋጀውን የሙዚቃ ኮንሰርት የካቲት 14 ቀን 2012ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የላዮን ፕሮሞሽንና
ኤቨንት ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታነህ አንዳርጌ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ ለህዝ የተመቻቸ እንዲሆንና የቁጥር መጠን የበለጠ ለማስተናገድ በማሰብ
በመስቀል አደባባይ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለማድረግ ማሰባቸውን የገለፁ ሲሆን የሙዚቃ ዝግጅቱን ለመታደም መደበኛ ሁለት መቶ ብር ቪአይፒ አምስት መቶ ብር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የድምፃዊውን ክፍያ እና የሚገኙ ታዳሚዎች የቁጥር መጠን ግምት ከመናገር ተቆጥነዋል፡፡ታዳሚው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ዝግጅቱ ስፍራ መግባት እንደሚችል የተናገሩት አቶ ጌታነህ ቴዲ አፍሮ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የሙዚቃ ስራውን እንደሚያቀርብ ተገልጧል፡፡


Read 12459 times