Saturday, 22 February 2020 10:26

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተገደሉ

Written by  ሰላም ገረመው
Rate this item
(1 Vote)

     ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን እያደንኩ ነው ብሏል
                    
             የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ፡፡ የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ዶ/ር ሰለሞን ትላንት ምሳ በልተው ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ወደ ቢሮአቸው ሲመለሱ ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት ሕይወታቸው አልፏል ብለዋል - ምንጮች፡፡ በአዛዡና ባልደረቦቻቸው ላይ ተኩሱን የከፈቱት የኦነግ ሸኔዎች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ቢጠቆምም ማረጋገጥ ግን አልተቻለም፡፡ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የከተማዋ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች በቅንጅት እየሰሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ኮሚሽነሩ የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ በመሆን
ከሁለት ዓመት በላይ ማገልገላቸው ታውቋል፡፡

Read 1662 times