Monday, 24 February 2020 00:00

‹‹የመንታ መንገድ ወግ›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

  በእውቁ ፖለቲከኛ ብርሃነ ፅጋብ የተፃፈውና ኢሕአዴግን ከውልደቱ አሁን ‹‹ብልጽግና ፓርቲ›› እስከተባለበትና ከውህዱ ፓርቲ ህወሃት እስካፈነገጠበት ድረስ በተለያዩ ክፍሎችና ምዕራፎች የሚተነትነው ‹‹የመንታ መንገድ ወግ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መጽሐፉ በአቶ መለስ ዜናዊ በተሰናዱት አምስት የስልጠና መጽሐፎች፣ ከህወሃት ጋር ስለነበራቸው ቆይታና ከለውጡ በኋላ ከድርጅቱ ርቀው የግል ሕይወታቸውን ሲመሩ ስለሚያስታውሷቸው የትግል ዘመኖች፣ ስለ ህወሃት ከብልጽግና ፓርቲ ማፈንገጥ፣ ስለ ኦህዴድና ሌሎች 5 አጋር ፓርቲዎች በስፋት የሚተነትን ሆኖ ‹‹ኑዛዜ›› እና ‹‹የስንብት ዋዜማ›› በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የተሰናዳ ሲሆን በስምንት ምዕራፎች ተከፋፍሎና በ230 ገጽ ተቀንብቦ በ180 ብርና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ፖለቲከኛው ፀሐፊ ብርሃነ ፅጋብ በቅርቡ ለንባብ ባበቁት ‹‹የኢሕአዴግ የቁልቁለት ጉዞ›› መጽሐፋቸው ይበልጥ ይታወቃሉ፡፡

Read 9813 times