Saturday, 29 February 2020 10:59

ምርጫ ቦርድ የኦዴፓ ቢሮዎች እንዲመለሱ ጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

    ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኢዜማ የሚጠቀምባቸውን የቀድሞ የኢዴፓ ቢሮዎች ቤቶች ኮርፖሬሽን ለባለቤቱ እንዲመልስ ጠየቀ፡፡
ኢዴፓ ህጋዊ ሰውነቱን በድጋሚ ካረጋገጠ በኋላ ከኢዜማ ጋር ውህደት የፈፀሙ የኢዴፓ አመራሮች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ቢሮዎች ይመለሱልኝ በሚል በፍ/ቤት ክስ መስርቶ የኢዜማን ምላሽ እየተጠባበቀ ባለበት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢሮዎቹ ለባለቤቱ ለኢዴፓ ሊመለሱ ይገባል ሲል ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ደብዳቤ መፃፉ ታውቋል፡፡
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለቤቶች ኮርፖሬሽን በፃፈው ደብዳቤ መሠረት በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለት የኢዴፓ ቢሮዎች እና በባህርዳር የሚገኝ አንድ ቢሮ ለኢዴፓ ሊመለስ ይገባል ብሏል፡፡
እነዚህ ሶስት ቢሮዎች በአቶ አዳነ ታደሰ የሚመራው ኢዴፓ ቢሮዎች መሆናቸው ታውቆ  ምርጫ ቦርድ ጠይቋል፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዙ ቀደም ሲል በአቶ አዳነ ታደሰ የሚመራው ኢዴፓ ቢሮዎቼ ይመለሱልኝ ሲል ኢዜማን በፍ/ቤት ከሶ የነበረ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም ተከሳሽ ጉዳዩን ቀርቦ እንዲያስረዳ ለመጋቢት 2 ቀን 2012 ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ለአዲስ አድማስ ማብራሪያ የሰጡት የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ በበኩላቸው ቤቶች ኮርፖሬሽን ቢሮዎቹን የሚያስረክበን ከሆነ ክሳችንን እናቋርጣለን ብለዋል፡፡

Read 1168 times