Print this page
Saturday, 29 February 2020 11:36

“ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን” የኪነ ጥበብ ዝግጅት አርብ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

    በሮያል የማስታወቂያ ድርጅት በየወሩ የሚሰናዳውና የትልልቅ ኢትዮጵያውያንን ስራና ታሪክ የሚዘክረው ‹‹ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን›› የተሰኘው የኪነ ጥበብ ዝግጅት የፊታችን አርብ የካቲት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በአገር ፍቅር ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዚህ ወር የሚዘከሩት ፊታውራሪ አመዴ ለማ ሲሆኑ ልጃቸው አቶ ካሱ አመዴ ለማ በክብር እንግድነት እንደሚገኙ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ በዚህ የኪነ ጥበብ መሰናዶ ኮሜዲያን አሰፋ ተገኝ፣ ገጣሚና ተዋናይ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድምፃዊያኑ ታረቀኝ ሙሉ፣ በእውቀቱ ሰውመሆን (ጉስም)፣ ኢየሩሳሌም  አስፋው (ጄሪ)፣ ወደሬ ታደሰ፣ ሞላ ካሳ (ሙለር ኮንሶ)፣ አንተነህ በፍቃዱ፣ ተስፋሁን ሀይሉና ሌሎችም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ መድረኩ በዋና አዘጋጁና አንጋፋው ጋዜጠኛ ሲመራ አጠቃላይ መርሃ ግብሩን አንጋፋው ጋዜጠኛ ይጥና ደምሴና ወጣቱ ጋዜጠኛ ኢዮብ አባተ እንደሚያስተባብሩትም ተገልጿል፡፡    

Read 11407 times
Administrator

Latest from Administrator