Saturday, 14 March 2020 11:01

“ሰርሳሪ ተረከዞች” መጽሐፍ ዛሬ በባህርዳር ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  የጋዜጠኛና ደራሲ የሺሃሳብ አበራ ሁለተኛ ስራ የሆነው “ኮርኳሪ ተረከዞች” መጽሐፍ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ ባህርዳር ከተማ በሚኘው ራህናይል ሆቴል ይመረቃል፡፡
በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የመጽሐፍ ዳሰሳን ጨምሮ ከመጽሐፉ የተቀነጨቡ ታሪኮች ለታዳሚ እንደሚቀርቡና ውይይት እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን፤ መጽሐፉ በዋናነት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትርክትና ስብራት ዙሪያ ትኩረት ማድረጉን ጋዜጠኛና ደራሲ የሺሃሳብ አበራ ተናግሯል፡፡
በ246 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ፣ በ136 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም “እንቧለሌ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡


Read 1585 times