Saturday, 14 March 2020 11:21

በአፋርና ኦሮሚያ አዋሣኝ በተፈጠሩ ግጭት በርካቶች ሞቱ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(8 votes)

      በአፋርና ኦሮሚያ አጐራባች፣ በግጦሽና በውሃ ምክንያት በተፈጠረ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ምንጮች ያስታወቁ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት የፀጥታ ሃይሎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ሐሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012 ቦርደዴ በተባለው ቦታ ሲሆን፤ ለሠአታት የቆየውን በተኩስ ልውውጥ የታገዘ ግጭት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጣልቃ ገብቶ ማረጋጋቱንም ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በግጦሽና በውሃ አጠቃቀም ሣቢያ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን የአካባቢው ምንጮች መንግስት በበኩሉ፤ የግጭቱ መንስኤ እየተጣራ መሆኑንና በግጭቱ ተሣታፊ የነበሩ ሃይሎችን ለህግ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በአፋርና በኦሮሚያ፣ በአፋርና በሶማሌ፣ በሱማሌና በኦሮሚያ፣ በአፋርና በአማራ ክልል አጐራባች አካባቢዎች በተደጋጋሚ በግጦሽና በውሃ ምክንያት ግጭቶች እንደሚፈጠሩ ይታወቃል፡፡

Read 12232 times