Saturday, 14 March 2020 13:33

በ9 ሴት ሰዓሊያን የተሰናዳ የስዕል አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 “አይደንቲቲ” የተባለው እና 25 ዓባላት ያሉት የሰዓሊያን ቡድን አባላት በሆኑት 9 ሴት ሰዓሊያን የተሰሩ ከ20 በላይ ስራዎች ለእይታ የቀረቡበት የስዕል አውደ ርዕይ ሐሙስ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል ተከፈተ፡፡
የስዕል አውደ ርዕዩ በዋናነነት ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8ን ምክንያት በማድረግ የተሰናዳ ሲሆን፤ ሁሉም ስዕሎች የሴቶችን ህይወት ፍልስፍና የአኗኗር ዘዴና ማህበረሰባዊ ጫና የሚያሳዩ እንደሆኑ ከተሳታፊዎቹ አንዷ ሰዓሊ ብርሃን በየነ ገልፃለች፡፡
በአብዛኛው ፈተና የሚሆንባቸው የስዕል ማሳያ ቦታ እንደሆነ የገለፀችው ሰዓሊዋ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ቦታ በነፃ ስለፈቀደላቸው አመሰግነዋል አወድ ራዕዩ ለአንድ ሳምንት ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

Read 21597 times