Saturday, 21 March 2020 12:59

ጃኖ “የቴክኖሎጂና ኢንቨስትመንት” ባንክ በምስረታ ላይ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

      ወረቀት ተኮር የሆነውን የባንክ አሠራር የሚያስቀርና የኢንቨስትመንትና ቴክኖሎጂ ባንክ የሆነው ጃኖ ባንክ በምስረታ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በምሁራን፣ በባንክ ባለሙያዎች፣ በነጋዴዎችና በኢኮኖሚስቶች አስተባባሪነት በምስረታ ሂደት ላይ ነው የተባለው ጃኖ ባንክ፤ ሙሉ ለሙሉ የዲጂታላይዜሽን አሠራርን ይዞ እንደሚመጣ ተጠቁሟል፡፡
ባንኩ አልሞ ከተነሳቸው የኢንቨስትመንት አገልግሎቶች መካከልም ከሌሎች ባንኮች ጋር በመተባበር ለግዙፍ ፕሮጀክቶች ብድር ማቅረብ፣ የግብርናውን ዘርፍ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ ብድር መስጠትና በጋራ ፕሮጀክት መስራት፣ ትልልቅና ጠቃሚ ሃሳብ ለያዙ ግለሰቦችና ድርጅቶች የብድር ድጋፍ ማቅረብ እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ማህበረሰብ በረጅም ጊዜ የሚከፈል የቤት መግዣ  የብድር አገልግሎት መስጠት ይጠቀሳሉ፡፡
የባንኩ የትኩረት አቅጣጫ ኢንቨስትመንትና ቴክኖሎጂ ከመሆኑ አንፃር ከተከፈለ ካፒታሉ ውስጥ 20 በመቶ ያህሉን ከድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር የጋራ ጥምረት በመፍጠር ለኢንቨስትመንት ያውለዋል፡፡  የባንኩን አክሲዮን መግዛት የሚፈልጉም ንግድ ባንክ፣ አባይ ባንክና አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ቀርበው መግዛት እንደሚችሉ አስተባባሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡

Read 4115 times