Saturday, 28 March 2020 11:26

ከኮሮና ስጋት ጋር በተያያዘ ስደተኞችና ተፈናቃዮችን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ያስፈልጋል ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

     7.8 ሚሊዮን ያህል ተረጅዎች ያሏት ኢትዮጵያ በአገሪቱ የወረርሽኝ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ታሳቢ ላደረገ የእርዳታ ስርጭት መዘጋጀት እንደሚገባ የረድኤት ድርጅቶች አሳሰቡ፡፡ መንግስት በርካታ ሰዎች እንዳይሰበሰቡ መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ እርዳታቸውን ሰብሰብ ብለው የሚቀበሉና በተጠጋጋ ሁኔታ በአንድ አካባቢ ሰፍረው ለሚገኙ ተረጂዎች ባለፉት ሳምንታት እርዳታ በአግባቡ ማድረስ እንዳልተቻለ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ አስታውቋል፡፡በቀጣይ መንግስት የኮሮና ስጋትን ታሳቢ ያደረገ የእርዳታ አቅርቦት መመሪያ እንዲያዘጋጅና ተፈናቃዮችንና ስደተኞችን ታሳቢ ያደረጉ የጤና ዝግጅቶችም እንዲደረጉ ተቋሙ ጠይቋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተለይ በርካቶች በጥግግትና በትፍፍግ አገልግሎት የሚያገኙባቸው የስደተኛ ካምፖችና የተፈናቃይ መንደሮች በእጅጉ ተጋላጭ መሆናቸውን የጠቆሙት የረድኤት ድርጅቶች፤ አዳዲስ ስደተኞችን መቀበልን በተመለከተም ተጨማሪ ግልጽ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ተጠይቀዋል፡፡ በጤና አገልግሎት አቅርቦትም ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን ታሳቢ ያደረጉ ዝግጅቶች እንደሚያስፈልጉም ተመልክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ9 መቶ ሺህ በላይ የኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማልያና ሌሎች ጎረቤት አገራት ስደተኞች በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡  

Read 1041 times