Saturday, 28 March 2020 16:16

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(11 votes)

ጥበብ
አትፅናኝ
ሞትን አንመልሰው፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ አይተናል መሰለሽ፤
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ፡፡
አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ምፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰው
ምን ይባላል ይኼ፤ ’ባንቺ የደረሰው?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነው እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ፡፡
በእድፋም ጥፍሩ፤ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድን ነው መማፀን?
ምንድን ነው ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነው ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ’ረም፡፡
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩምትር በይ - ዋኔ፤
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ፡፡
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነው፤ አንቺን የሚያፅናናሽ!
(ከመዘክር ግርማ “ወደ መንገድ ሰዎች”
የግጥም መድበል)


Read 3120 times