Saturday, 04 April 2020 11:27

የኮሮና ቫይረስ ሕመም ከእርግዝና ጋር በተገናኘ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

   በአሁኑ ጊዜ ወረርሽኙ ዓለምን ያስጨነቀው በ2019 የተነሳው የኮሮና ቫይረስ ስያሜው (COVID-19) ነው፡፡ ይህ ቫይረስ ከአሁን ቀደም በአለም ላይ የተከሰቱ ዝርያዎች የነበሩት ሲሆን ስያሜያ ቸውም SARS-CoV- እና MERS-CoV የተሰኙ ናቸው፡፡
SARS-CoV---severe acute respiratory syndrome MERS-CoV-----MERS: Middle East respiratory syndrome በመባል ስያሜ ተሰጥ ቶአቸው የነበሩት ቫይረሶች በተከሰቱባቸው ወቅቶች የተለያዩ ጉዳቶችን አድርሰው እንደነበር መረጃዎቹ ይጠቁማሉ፡፡
እርግዝናን በሚመለከት ቀደም ሲል ተከስተው ከነበሩት የኮሮና ቫይረሶች መማር የሚገባን ነገር ካለ እና እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ምን ጥንቃቄ ቢያደርጉ ይመከራል የሚለውን ለመጠቆም መነሻ እንዲሆን ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኞች ሁኔታ ከአሜሪካው የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ጆርናል American Journal of Obstetrics and Gynecology (2020), ያገኘ ነውን ነጥብ ታነቡ ዘንድ ጋብዘናል ፡፡
SARS-CoV- የተባለው ኮሮና ቫይረስ በእርግዝና ላይ ያስከተለው ተጽእኖ
በመተንፈሻ አካል ላይ ህመም የሚያስከትለው SARS የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዘር በእርጉዝ ሴቶች ላይ የሚያስከትለውን ችግር በሚመለከት ህመሙ በተከሰተበት ወቅት በተሰራጨባቸው አገራት የነበረውን ሁኔታ የአሜሪካን የማህጽንና ጽንስ ሕክምና ማህበር ጆርናል ሙሉ በሙሉ መረጃ አግኝተናል ባንልም የደረስንበትን አቅርበናል በሚል ለንባብ ብሎታል፡፡ SARS-CoV በሚል ስያሜ የተጠ ራው ኮሮና ቫይረስ እ.ኤ.አ ፌብረዋሪ 2003/ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና Guang- dong  ጉዋንግዶንግ በተባለው ግዛት የተገኘ ሲሆን ይህ ቫይረስ በጊዜው በአለም ወደ 30 በሚጠጉ ሀገራት ተሰራጭቶአል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የተገኘው መረጃም ወደ 8000/ሺህ ታማሚዎች መገኘታቸውንና ከእነዚህም ወደ 700 የሚሆን ሞት የተመዘገበበት ነበር፡፡ ይህ SARS የተባለው ኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዲ ገታ የተደረገውም በህብረተሰብ ጤና ተቋማት አማካኝነት ሰዎች ለሰዎች በተለይም ቫይረሱ ካለባቸው ጋር የሚያደርጉትን ንክኪ እንዲያቋርጡ ወይንም እንዲቀንሱ በመደረጉ ነው፡፡ ይህ እርምጃም የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እ.ኤ.አ በ2004/ ዓ/ም ጭርሱንም እንዳይኖር አስች ሎታል:: SARS የተሰኘው ኮሮና ቫይረስ ትኩሳት ያለው፤ ራስምታት፤ከፍተኛ ሕመም፤ተቅማጥ የመሳሰሉት ከባድ ሕመሞች የሚታዩበት ነበር፡፡ ሕመሙ ባጋጠ መበት ቦታም ይሁን በየትኛውም ሰዎች በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ በቂ አየር ከ9-10 ከመቶ እንዲሆን ይመከር የነበረ ሲሆን ቫይረሱም ከ9-10 ከመቶ የሚሆን የሞት አደጋን ያስከትል ነበር፡፡
SARS-CoV ለተባለው ኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት ከሚባሉት ውስጥ በአገራችን የሌሊት ወፍ ተብለው የሚጠሩ እንዲሁም ከቤት ውጭ የሚኖሩ አንዳንድ የድመት እና የውሻ ዝርያ ዎች ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶአል፡፡
ስርጭቱ ግን ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር በእጅ በመነ ካካት እንዲሁም በማስነጠስ ወይንም በመሳል ጊዜ የሚፈናጠሩ ጠብታዎች ወደ ደህናው ሰው የሚረጩ ከሆነ የሚተላለፍ መሆኑ ተነግሮ ነበር፡፡ በንግግር ወቅት በአየር አጉዋጉዋዥነት ከታመመው ሰው ወደ ደህናው ሰው ቫይረሱ የሚረጭ ከሆነ በሽታው እንደሚተላለፍ እና ማንኛውም ሰው በተገቢው መንገድ እራሱን እንዲከላከል ለህብረተሰቡ መልእ ክት በመተላለፉ ብዙዎች እራሳቸውን ለማዳን ችለዋል፡፡ አንድ ሰው በዚህ ቫይረስ መያዙን የሚያውቅበት ጊዜ ከ4-6 ከዚያም ካለፈ ከ2-14 ቀናት ነበሩ፡፡  
SARS ከተሰኘው ቫይረስ ጋር በተያያዘ በሆንግ ኮንግ 12 እርጉዝ ሴቶች ወደ ሕክምና የሄዱ ሲሆን ከእነሱ መካከልም አስከፊ ችግር ደረሰባቸው የሚባሉት 25 ከመቶ እንደነበሩ የአሜሪካ የማህጸንና ጽንስ ህክምና ጆርናል ይገልጻል፡፡  ጆርናሉ እንደሚያስነብበውም የህክምና ክትት ላቸው እና የላቦራቶሪ ውጤታቸው ግን እርጉዝ ካልነበሩ ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ እርግ ዝናው በሶስት ደረጃ የተከፋፈለ ሲሆን እስከ ሶስት ወር ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ይባላል፡፡ ከሶስት እስከ ስድስት ወር ድረስ ደግሞ ሁለተኛው ደረጃ ሲሆን ከስድስት ወር ሰ,እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ ሶስተኛው ደረጃ በመባል ታወቃል፡፡በ SARS ጊዜ እርግዝናቸው በመጀመ ሪያው ዙር ማለትም እስከሶስት ወር ድረስ ባለው ጊዜ ከታመሙት ከሰባቱ ሴቶች አራቱ በድንገት ውርጃ የገጠማቸው ሲሆን ሁለቱ እርግዝናቸው ተቋርጦአል (ጽንሱ ሕይወት አጥቶአል)፡፡ እርግዝ ናቸው 24 ሳምንት ከሞላው ከአምስቱ ሴቶች መካከል አራቱ ጊዜው ያልደረሰ ልጅ ወልደዋል፡፡ በ SARS ቫይረስ በመያዛቸው ምክንያት በተፈጠረው አንዳንድ የጤና ሁኔታ በ26ኛው፣28ኛው እና 32ኛው ሳምንት በቀዶ ሕክምና ጤነኛ እና የተሟላ ክብደት ያላቸውን ልጃቸውን የወለዱ ሴቶችም ነበሩ፡፡ በእርግጥ አንዳንድ የመተንፈሻ አካል ችግር የደረሰባቸውና በሁዋላም የብሮንካ ይትስ ችግር የገጠማቸው ልጆች እንደነበሩ ሪፖርት ተደርጎአል፡፡     
MERS የተባለው ኮሮና ቫይረስ በእርግዝና ላይ ያስከተለው ተጽእኖ
Middle East Respiratory Syndrome MERS-CoV የተባለው የሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ በመጀመሪያ የተከሰተው በሳኡዲ አረቢያ ሲሆን ጊዜውም እ.ኤ.አ 2012/ዓ/ም ነበር፡፡ ይህ ቫይረስ በአረቢያን ፔንሱላ እና እየዋለ እያደረም ከአረቢያን ፔንሱላ አሜሪካንን ጨምሮ ወደ ሌሎች አገሮች ተስፋፍቶ ነበር፡፡  ከአረቢያን ፔንሱላ ውጪ በከፍተኛ ሁኔታ ሕመሙ ተስፋፍ ቶባቸው ከነበሩት መካከል ኮሪያ ዋናዋ ነበረች፡፡ በኮሪያ እ.ኤ.አ በ2015 ወደ 2.500 ሰዎች በቫይረሱ የታመሙ መሆናቸው እና ወደ 860 የሚሆኑ ሞቶች እንደተመዘገቡ መረጃው ይጠቁማል፡፡ የሞት መጠኑ ከ35-40 ከመቶ የደረሰ ነበር፡፡ MERS-CoV የያዛቸው ሰዎች በእድሜያቸው 50 አመት የደረሱ ሲሆን  ወደ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ወንዶች ነበሩ፡፡ MERS-CoV የተባለው ቫይረስ የህብረተሰብ ጤና ተቋማት ባደረጉት ጥረት እ.ኤ.አ ከ2016/ ወዲህ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአሜሪካ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ጆርናል ይገልጻለ፡፡
ጆርናሉ እንደሚገልጸው MERS-CoV ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የነበረው ሁኔታ ምን ይመስል እንደነበር የሚጠቁም ግልጽ የሆነ መረጃ በተገቢው መንገድ እንዳልተገኘ እና ውስን እንደሆነ ነው፡፡ MERS-CoV እና SARS-CoV ከሌላው ሰው በተለየ በእርግዝና ላይ ባሉ ሴቶች ላይ ያደረሱት ምንም የተለየ ጉዳት የለም ሊያሰኝ ቢያስችልም ግን በግልጽ መልስ ሊያገኝ የሚገባው ስለሆነ በአሁኑ ወቅት አለምን በማስጨነቅ ላይ ያለው COVID-19 ኮረና ቫይረስ ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የሚያደርሰውን ጉዳት መከታተል ያስፈልጋል፡፡
COVID-19 የተባለው ኮሮና ቫይረስ በእርግዝና ላይ ያስከተለው ተጽእኖ
እ.ኤ.አ ዲሴምበር 31/2019 በውሀን ቻይና መከሰቱ የተገለጸው COVID-19 ኮረና ቫይረስ በዲሴ ምበር እና በጃንዋሪ መካከል 44 ያህል ሰዎች ብቻ መያዛቸው ነበር የተገለጸው፡፡ ጃንዋሪ 7 /2020 የቻይና መንግስት የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ይፋ ካደረገ በሁዋላ ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት በቻይና ሌሎች ግዛቶች እና ወደሌሎች አገሮችም መዛመቱን ቀጠለ፡፡     
ቫይረሱ መሰራጨት ከጀመረ ከሶስት ወር ባልበለጠ ጊዜ የታማሚዎች ቁጥር በአለም ዙሪያ በመቶ ሺዎች በመድረሱ ስርጭቱ የሚያበቃበትን ጊዜ መገመት እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ይህንን የወረርሽኝ በሽታ ለመቋቋም የህብረ ተሰብ ጤና እና የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ግብአቶቻቸው ምን ያህል የተሟሉ ናቸው የሚለውን ጥያቄ ከአገር አገር ያለው የተለያየ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መልስ ለመስጠት ያስቸግራል፡፡
በአለም ዙሪያ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች አዲስ ሕይወትን ወይንም ትውልድን ለአለም የሚያስ ረክቡ በመሆኑ ልዩ ትኩረትና ጤንነታቸውም በአግባቡ ሊጠበቅላቸው እንደሚገባ አለም አቀፉ ህብረተሰብ የሚረዳው ነው፡፡ በእርግዝና ምክንያት ሊኖሩ የሚችሉ አንዳንድ የጤና ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምን ያህል ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ክትትል በሚያደርጉላቸው የህክምና ባለሙያዎች ያላሰለሰ ምክር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡  
እንደዚህ ያሉ አለምን የሚያስጨንቁ ወረርሽኞች ሲከሰቱ በእርግዝና ላይ ላሉ ሴቶች ልዩ ትኩ ረት መስጠት እና እናቶችንም ሆነ የወደፊት አለምን መቀጠል እውን የሚያደርጉ ጽንሶችን የማዳን ስራ ቸል ሊባል የማይገባ መሆ ኑን የአሜሪካ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ጆርናል ያስረዳል፡፡


Read 13601 times