Saturday, 04 April 2020 11:40

የባልደራስ ወጣቶች አርአያነት ያለው ተግባር

Written by 
Rate this item
(2 votes)


             በአዲስ አበባ በተለምዶ ባልደራስ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ወጣቶችና በጐ ፈቃደኞች በኮሮና ወረርሽኝ የ250ሺህ ብር ድጋፍ አሰባስበው ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ጽ/ቤት አስረክበዋል፡፡ ከ30 በላይ የሚሆኑት የአካባቢው በጐ ፈቃደኛ ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት አርአያነት ያለው ተግባር ማከናወናቸውን ለአዲስ አድማስ ያስረዱት የወረዳ 7 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መገርሣ ገላና በዚህ ድጋፍ የተሰባሰበው ቁሳቁስ ምናልባት እንቅስቃሴ ቢገታ አቅም ለሌላቸው ድጋፍ የሚውል ነው ብለዋል፡፡
ወጣቶቹ በዚህ ድጋፍ ማህበረሰብ በአጠቃላይ ግምቱ 25ሺህ ብር የሆነ 50 ኩንታል መኮረኒና ፓስታ፣ ከ3 መቶ በላይ ንፅህና መጠበቂያ ሣሙና እና ሌሎች ቁሳቁሶች፣ ዘይት፣ ሩዝ መገኘቱን ዋና ስራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል፡፡ የአካባቢው ወጣቶችና በጐ አድራጊዎች ድርጊት በእጅጉ የሚደነቅና ለሌሎች አካባቢዎችም አርአያነት ያለው መሆኑን አቶ መገርሣ ገላና አስገንዝበዋል፡፡


Read 1831 times