Saturday, 04 April 2020 11:44

ጋዜጠኛ ያየሰው ሺመልስ ከእስር እንዲለቀቅ ሲፒጄ ጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

  የተሳሳተ መረጃ አሰራጭቷል በሚል የታሠረውን ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈታው አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ) ጠየቀ፡፡ የ“ፍትህ” መጽሔት አምደኛ እንዲሁም በትግራይ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው “ኢትዮ ፎረም” ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ያየሰው፤ ከኮሮና ጋር በተያያዘ “መንግስት 2መቶ ሺህ የመቃብር ስፍራ እንዲዘጋጅ አዘዘ” የሚል ዜና ማሠራጨቱን ተከትሎ፣ ህዝብን የሚያሸብር የተሳሳተ መረጃ አሠራጭቷል በሚል መታሠሩን የሲፒጄ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ ጋዜጠኛው ለገጣፎ ከሚገኘው የዘመዱ መኖሪያ ቤት፣ በፀጥታ ሃይሎች ተወስዶ ከታሠረ በኋላ፣ ፍ/ቤት ቀርቦ ለፖሊስ ተጨማሪ የ6 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደተፈቀደለት ታውቋል፡፡ “በዚህን ወቅት ጋዜጠኞችን ሪፖርት ባደረጉት ጉዳይ ለእስር መዳረግ ላልተገባ ሳንሱር ይዳርጋል ያለው ሲፒጄ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛውን በአስቸኳይ እንዲፈታ እንዲሁም ሌሎች ጋዜጠኞችም በሚዘግቡት ጉዳይ እስር እንደማያጋጥማቸው ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቋል::


Read 2648 times