Print this page
Saturday, 18 April 2020 14:46

ኮሮና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በእጅጉ ይጎዳል ተባለ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

   በዘንድሮ አመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገት በኮሮና ወረርሽኝ ተያይዞ በሚመጡ ሁኔታዎች ምክንያት ወደ 3.2 በመቶ እንደሚያሽቆለቁል አይኤምኤፍ የተነበየ ሲሆን መንግስት በበኩሉ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በ5 በመቶ ያድጋል ብሏል፡፡
ባለፈው አመት ማለትም በ2011(2019) የኢትዮጵያ አመታዊ አጠቃላይ እድገት (GDP) 9.0 በመቶ እንደነበር ያስታወቀው አለማቀፍ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ዘንድሮ ኮሮና ሊያስከትል በሚችለው ጫና ምክንያት እድገቱ ወደ 3.2 በመቶ ያሽቆለቁላል ብሏል፡፡
ይህ የእድገት ምጣኔ በቀጣይ አመት 2013(2021) መነቃቃት ያሳያል ወደ 4.3 በመቶው ከፍ ይላል ብሏል - አይኤምኤፍ በሪፖርቱ፡፡
ከኢትዮጵያ በመቀጠል ባለፈው አመት 2019 ላይ ከፍተኛ እድገት የነበራቸው ኮትዲቯር፣ ታንዛኒያ፣ ጋና እና ኬኒያም ዘንድሮ እጅግ ዝቅተኛ እድገት ይኖራቸዋል ብሏል - ሪፖርቱ የኮትዲቯር አመታዊ አጠቃላይ እድገት ከ6.9 በመቶ ወደ 2.7፣ የታኒዛኒያ ከ6.3 በመቶ ወደ 2 በመቶ የጋና ከ6.1 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ እንዲሁም የኬንያ ከ5.6 በመቶ ወደ 1 በመቶ እንደሚያሽቆለቁል ሪፖርቱ አትቷል፡፡
በርካቶቹ የሠሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራትም ከ0 በታች እድገት በአመቱ እንደሚያስመዘግቡ ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
መንግስት በበኩሉ በዘንድሮ የ2012 ዓ.ም የ9 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ አቅዶ እንደነበር የገለፀ ሲሆን፤ አሁን ላይ ግን ይህ እቅድ እንደማይሳካና እድገቱ ከ4 እስከ 5 በመቶ ባለው ተወስኖ እንደሚቆይ አስታውቋል፡፡

Read 10774 times
Administrator

Latest from Administrator