Saturday, 09 May 2020 12:25

አቶ በረከት ስምዖን የ6 ዓመት፣ አቶ ታደሰ የ8 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

   ከጥረት ኮርፖሬት ሀብት ምዝበራ ጋር ተያይዞ የሙስና ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ፤ የ6 ዓመትና የ8 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው፡፡
ሁለቱ የቀድሞ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጥረት ኮርፖሬት የቦርድ አመራሮች በነበሩበት ጊዜ ተቋሙን በማያመች አኳኋን በመምራት፣ ለምዝበራ ዳርገዋል በሚል የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው፣ ላለፈው አንድ አመት ተኩል ጉዳያቸውን በባህር ዳር በእስር ላይ ሆነው ሲከታተሉ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በአቶ በረከት ስምዖን ላይ በሁለት ክሶች እንዲሁም በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ በሶስት ክሶች የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላለፈባቸው ሲሆን ትናንት ፍ/ቤቱ አቶ በረከት ስሞዖን በ6 ዓመት እስርና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲሁም አቶ ታደሰ ካሳ በ8 ዓመት እስራት በ15 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡
ከእነ አቶ በረከት ጋር ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት አቶ ዳንኤል ግዛው በነፃ መሰናበታቸው ታውቋል፡፡


Read 10070 times