Saturday, 16 May 2020 11:52

የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ በኋላ 11ሺህ 8 መቶ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

 የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ባሉት የ1 ወር ከሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ 11ሺህ 8 መቶ ኢትዮጵያዊያን ከስደት መመለሳቸውን አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ፡፡
አይኦኤም ስደተኞች እና የኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ጥረትን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ፤ ከመጋቢት 23 ቀን 2012 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የተሰደዱ 11ሺህ 8 መቶ ኢትዮጵያውያን በየሀገራቱ አስገዳጅ እርምጃ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብሏል፡፡
ከተመላሾቹ መካከል 3 ሺህ ያህሉ ከሳውዲ አረቢያ፣ 3ሺ827 ከሱዳን፣ 3ሺ 332 ከጅቡቲ፣ 1ሺ 336 ከሶማሊያ እንዲሁም 505 ከኬንያ መሆናቸው ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
ከእነዚህ የስደት ተመላሾች መካከል 5ሺህ 175 ያህሉ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ማረጋገጡን የገለፀው አይኦኤም፤ ስደተኞች በእጃቸው ምንም የሌለ በመሆኑ አስፈላጊው የምግብ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብሏል፡፡

Read 11358 times