Saturday, 30 May 2020 11:41

ዴምህት ለትጥቅ ትግል በድጋሚ ኤርትራ መግባቱ ተነገረ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) የህወኃትን አካሄድ በመቃወም በድጋሚ የትጥቅ ትግል ለመቀጠል ወደ ኤርትራ መግባቱን ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የዛሬ 2 ዓመት ግድም ከበርካታ ድርድር በኋላ የትጥቅ ትግል አቁሞ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በክልላዊ ጉዳዮች ላይ ከህወኃት ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱ የሚነገርለት ዴምህት፤ በአሁን ወቅት ህወኃት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የያዘው አቋም የማልስማማበት ነው በማለት በድጋሚ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ኤርትራ ገብቷል ተብሏል፡፡ ህወኃትንና ዴምህትን በዋናነት ያቃረናቸው ጉዳይም ህወኃት ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ሀሳብ እያራመደ መምጣቱ እንደሆነ ኤርትራ የገቡት የዴምህት አባላት መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተን የፖለቲካ አላማ እንደሌለው የገለፀው ዴምህት፤ በዚህ አቋሙም በርካታ አባላትና አመራሮቹ በትግራይ ታስረው እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡
ለትጥቅ ትግል ወደ ኤርትራ የገቡት የዴምህት አባላት ምን ያህል እንደሆኑ በዘገባው የተባለ ነገር የለም፡፡

Read 2521 times