Print this page
Saturday, 30 May 2020 13:21

ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በኤሌክትሮኒክስ ትምህርት መስጠት ጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን በኤሌክትሮኒክስ የትምህርት አሰጣጥ መተግበሪያ መድረኮች (Online Learning platforms) በመታገዝ ማስተማር መጀመሩን ገለፀ፡፡
የ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ትምህርት ባቆሙበት በዚህ ወቅት ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ገጽ ለገጽ ይሰጡ የነበሩ የትምህርት መርሃ ግብሮች በጥሩ ሁኔታና ውጤት እንዲጠናቀቁ በማሰብ በኤሌክትሮኒክስ የትምህርት አሰጣጥ መተግበሪያ መድረኮች በመታገዝ ከሚያዝያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ማስተማር መቀጠሉን አስታውቋል፡፡
ኮሌጁ ይህንን የኤሌክትሮኒክስ ትምህርት አሰጣጥ የበለጠ ለማሳካትና ውጤታማ ለማድረግም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ልምድ ያዳበሩ መምህራን በተጨማሪ፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ብቁ መምህራንን በመቅጠር የመማር ማስተማሩ ሂደት በተሳለጠ ሁኔታ መቀጠሉን ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ ጠቁሟል፡፡
የኤሌክትሮኒክስ ትምህርት አሰጣጥ መድረኩን ለማሳካትም፣ “Zoom video conferencing and melimu E-learning management system” የተሰኙትን ሁለት ዓይነት የመማሪያ መድረኮች መርጦ አዘጋጅቷል፡፡
የመማሪያ መድረኮቹም ለተማሪዎቹ በርካታ ጠቀሜታዎች የሚያስገኙ ማለትም በኦንላይን ገጽ ለገጽ ክፍል ገብቶ መከታተል የሚያስችሉ፤ በቪዲዮ እየታገዙ ትምህርትን መከለስ የሚያስችሉ፣ ከመምህሩ ጋር ሃሳብ መለዋወጥና በቡድን ውይይት መካፈል የሚያስችሉ እንዲሁም ከመምህሩ የቤት ስራ ቀጥታ መውሰድና ሰርቶ መመለስ የሚያስችሉ እንደሆኑ ታውቋል፡፡
ኮሌጁ ይህንን የኦንላይን ትምህርት ለተማሪዎቹ ሲሰጥ ምንም አይነት ክፍያ የማይጠይቅ ሲሆን ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለማለፍ ትልቅ መፍትሔ በመሆኑ ሌሎች ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች የኮሌጁን ተሞክሮ ወስደው ለተማሪዎቻቸው ቢተገብሩት ጠቀሜታው ትልቅ ይሆናል ብለዋል ሃላፊዎቹ፡፡  


Read 16496 times