Saturday, 06 June 2020 14:13

እስከ ህዳር ከ8.5 ሚ. በላይ ሰዎች በኮሮና ሊያዙ ይችላሉ ተባለ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(20 votes)

 ከ26ሺ በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚሞቱ ተገምቷል
                        
               በአገራችን የኮቪድ - 19 ወረርሺኝ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው በመጪው ህዳር ወር ላይ እንደሚሆን የተጠቆመ ሲሆን ከ8.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚያዙና ከ26ሺ በላይ የሚሆኑ በቫይረሱ ህይወታቸውን እንደሚያጡ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በቅርቡ ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው፤ የኮቪድ 19 ጥናቱ ያመለክታል፡፡ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርስበት ጊዜ ሰኔ ወር መጀመሪያ ገደማ መሆኑ ቀርቶ  ወደ መጪው ህዳር ወር 2012 ዓ.ም መገፋቱ ተጠቁሟል፡፡ በዚሁ መሠረትም ህዳር ወር 2013 መጀመሪያ አካባቢ 8 ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ አንድ ሺ አስራ አንድ ሰዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሲሆን፤ በዚሁ ወር አጋማሽ ላይ የሟቾች ቁጥር 26ሺ አምስት መቶ አርባ አራት እንደሚደርስ ጠቁሟል፡፡
የቫይረሱ ስርጭትና የሞት መጠን በምስራቅ አፍሪካ አገራት በፍጥነት እየጨመረ፣ ያመላከተው መረጃው፤ በኢትዮጵያ በሳምንቱ የበሽታው የስርጭት መጠን በ78% የሞት ምጣኔው ደግሞ በ61% ጨምሯል ብሏል፡፡ ከበሽታው የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱንም ከጥናቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
የበሽታው የስርጭት መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደርሳል ተብሎ በሚጠበቅበት የህዳር ወር ላይ 392ሺ767 የሆስፒታል አልጋዎችና 21ሺ038 የጽኑ ህመምተኛ አልጋዎች እንደሚያስፈልጉ የተነበየው የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጥናት፤ በሽታው እስከ ፈረንጆቹ አዲስ አመት ድረስ እንደሚቆይና እስከዚያው ጊዜ ድረስም በአጠቃላይ ከ50ሺ በላይ ሰዎች በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ አመልክቷል፡፡


Read 19424 times