Saturday, 14 July 2012 00:00

..ሐረር...አንድ ሆስፒታል...አምስት ሳተላይት ክሊኒኮች

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

በሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ሀምሳ አራት እናቶች ከተወለዱ ሕጻናት መካከል ሁለቱ ብቻ ናቸው ቫይረሱ የተገኘባቸው፡፡

(PMTCT) ኤችአይቪ ኤይድስ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ በሐረር አንድ የግል ሆስፒታል ከአምስት ሳላይት ክሊኒኮች ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ መሆኑን የአምዱ አዘጋጆች ለመመልከት ችለዋል፡፡ ሆስፒታሉ ሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ሲሆን የጽንስና ማህጸንን ሕክምና ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለሕብረተሰቡ በመስጠት ላይ የሚገኝ የግል ሆስፒል ነው፡፡ በሐረር ይማጅ ሜዲካል ሴንተር የተባለ የግል ሆስፒታልም ለዚህ አምድ ተጋብዞአል፡፡

በሁለቱም ሆስፒታሎች በመገኘት የህክምና ባለሙያዎቹንና በቅርብ ከሕመምተኞቹ ጋር የሚሰሩ ነርሶችን እንዲሁም ሳላይት ክሊኒክ ከሚ ባሉት ውስጥ የአንዱን ክሊኒክ ኃላፊ አስተያየት ለንባብ አቅርበናል፡፡ የሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አየለ ኃይሉ እንደተናገሩት...

.....ሆስፒታሉን ለየት ከሚያደርጉት አገልግሎቶች መካከል ሲቲ ስካን የተባለውን ሳይንሳዊ መሳሪያ በማስገባት አስፈላጊ የሆነውን ሕክምና በምስራቁ በኩል ላሉ ታካሚ ዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በአስራ አምስት ቀን ወደሆስፒታሉ በሚመጣ ፓቶሎጂስት አማካ ኝነትም ሕክምና  በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም ምክንያት የታካሚዎች ወደአዲስ አበባ የመሄድ አስፈላጊነት በእጅጉ ቀንሶአል ማለት ይቻላል፡፡ የሓልማ አገልግ ሎትን በሚመለከትም ገና የሚወለዱ ሕጻናትን ከኤችአይቪ ቫይረስ ለመከላከልና የእናቶችንም ሞት ለመቀነስ የሚያስችል አገልግሎት በመሰጠት ላይ ሲሆን ምንጊዜም በሆስፒታሉ አንድ ባለሙያ እንዲገኝና ካሉት ስድስት አዋላጅ ነርሶች ጋራ በመሆን ሕክምናውን እንዲሰጥ የሚያስችል አሰራር በመከተል ላይ እንገኛለን፡፡..ብለዋል፡፡

በሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ማዋለጃ ክፍል ያገኘናት ሲ/ር አለምነሽ ዳበሳ ከፊቷ በተዘረጋው ትልቅ መዝገብ ላይ አተኩራ ስራዋን በመስራት ላይ እንዳለች ነበር አንዳንድ ነጥቦችን ያነሳንላት፡፡ እንደሲስተርዋ ማብራርያ፡-

.. ይሄ ከፊት ለፊ የተዘረጋው መዝገብ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች ጋር በተያያዘ ክትትል ያላቸው ሕጻናትና መከላከሉ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ይመዘገባሉ፡፡ እናቶች ለክትትል በሚመ ጡበት ጊዜ ከቫይረሱ ጋር መኖር ያለመኖራቸው ሁኔታ ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ የመጣ ነው፡፡ በእርግጥ ቀደም ባሉት ጊዜያት በግል ሆስፒታሎች ይህ አገልግሎት የማይሰጥ እንደነበረ የሚ ታወስ ነው፡፡ ምንያቶቹም የተለያዩ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አደረጃጀት አለመኖሩና አንዳንድ ጊዜም የግል የጤና ተቋማቱ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ ላይ ያተኩሩ ስለነበር ነው፡፡ በዚህ አሰራር ቢቀጥል ኖሮ ብዙ እናቶችን የሚያሳጥን ሲሆን አሁን ግን በተለይም በዚህ ሆስፒታል ከኢሶግ ጋር በመተባበር ስራውን ለመስራት የጽ ንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎቹ ሙሉ ፈቃደኛ በመሆናቸው በተሻለ ሁኔታ አገልግ ሎቱን መስጠት ተችሎ አል፡፡ ስለሆነም በሌሎች ችግሮች ካልሆነ በስተቀር አንዲትንም እናት አጥተን አናውቅም፡፡ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለውን አሰራር በምንም ምክንያት እንዳይቋረጥ ከማድረግ ባሸገር ምና ልባት ሁኔታውን ካለ መረዳት አገልግሎቱን ችላ ብለው የሚሄዱ እናቶች እንኩዋን ቢያጋጥሙን በልመና ጭምር አሳምነን ስራውን እንሰራለን፡፡..

በመቀጠል ያመራነው ይማጅ ወደተባለው የግል ሆስፒታል ነው፡፡ ሆስፒታሉ ጠቅላላ ሆስፒታል ሲሆን ባለቤቱ አቶ ሳብሪን አህመድ ይባላሉ፡፡ ሆስፒታሉ ሐረር ውስጥ ስራ የጀመ ረው እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2001/ዓም ነው፡፡ አቶ ሳብሪን የሆስፒታሉን የሓልማ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለውን ስራ በሚመለከት የሚከተለውን ብለዋል፡፡

.. ኤችኤቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለውን ስራ የጀመርነው ከሶስት አመት ወዲህ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን ይህንን ስራ ለመስራት የቡድን ስራ ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህም ማለት መንግስትም ሆነ የግል ተቋማቱ ተለያይተን ለየብቻችን ልንሰራው የምንችለው ስላልነበረ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ በጤና ቢሮ በኩል የነበረው ሁኔታ ብዙም ስራውን ለመጀመር የሚያበረታታ አልነበረም፡፡ ከዚያ በሁዋላ ግን ስራውን ለመስራት በሚያስችል ሁኔታ ከስልጠና ጀምሮ አቅርቦቱን በማስተካከል ልንሰራ የምንችልበትን መስመር የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እንዲሁም የጤና ቢሮው ከእኛ ጋር በመቀናጀት መስራት በመቻላችን ብዙ እናቶችን ማከም እንዲሁም ሕጻናቱ ከቫይረሱ ነጻ እንዲሆኑ የሚያስችለውን መንገድ በመከተል ላይ እንገኛለን፡፡..

በይማጅ ሆስፒታል ስራውን እየተዘዋወርን በተመለከትንበት ወቅት በስራ ላይ ያገኘናት ሲስተር ሙሉብርሀን ፋንታሁን በተለይም ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ እናቶች የተወለዱ ህጻናትን የመጨረሻ ውጤት ለማግኘት ሊደረግ የሚገባውን ትኩረት በሚመለከት ቤተሰብ ምንያህል ተግባራዊ እያደረገ ነው ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን መልስ ሰጥታለች፡፡

.. ... በእርግጥ ሕክምናቸውን ሌላ የጤና ተቋም ጀምረውም ይሁን በቀጥታ እዚሁ ክትትል ከሚያደርጉት እናቶች መካከል ምናልባት ከሰላሳው አንድ ወይንም ሁለት ሴቶች ቫይረሱ በደማቸው ሊገኝ ይችላል፡፡ ከዚህ ሁኔታ ስንነሳ በአሁን ወቅት ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ እናቶች ብዙም አይደሉም ማለት ይቻላል፡፡ ቢሆንም ግን ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ እናቶች የሚወለዱ ሕጻናትን ከቫይረሱ ነጻ ናቸው የሚለውን ማረጋገጫ ለመስጠት ከተ ወለዱ በሁዋላ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን ...እዚህ ላይ ግን ክፍተት አለ፡፡ አብዛኛዎቹ እናቶች የመጀ መሪያውን አርባ አምስት ቀን ሆስፒታሉ በሰጣቸው የጊዜ ቀጠሮ መሰረት ይገኛሉ፡፡ በዚያ ጊዜ ውስጥ ህጻኑ ለጊዜው ምንም ነገር የሌለበት መሆኑ ሲነገ ራቸው ከዚያ በሁዋላ ወደሆስፒታሉ መመለስ የማይፈልጉ ብዙዎች ናቸው፡፡ በእር ግጥ በጊዜው ሲመረመር ነጻ ነው ማለት የመጨ ረሻው እንዳልሆነና በእርግጠኝነት ማወቅ የሚቻልበትን ጊዜ እንዲሁም ሕጻኑ በተወሰነ ጊዜ ወደሆስፒታል መምጣት አንዳለበት ቢነገራቸውም ብዙዎቹ በመጀመሪያዎቹ አርባ አምስት ቀን የተሰጣቸውን መልስ በመ ያዝ በዛው የመቅረት ሁኔታ ይታያል፡፡ በእርግጥ አንዱ ምክንያት የአድራሻ መራቅ እን ደሆነ እንረዳለን፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ብዙ ጊዜ የሚሰጡን የስልክ አድራሻ የተሳሳተ ስለሚ ሆን በምንቀበላቸው የስልክ ቁጥር ስንሞክር አይገኙም ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ መሆናቸውን ባሎቻቸው እንዲያውቁባቸው ስለማይፈልጉ እንድናነጋግራ ቸውም የማይፈልጉ ብዙዎች ናቸው፡፡ የምክር አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ ባሎቻቸው እንዲቀርቡ ቢነገራቸውም ፈቃደኛ የማይሆኑና ችግሩን እራሳቸው እንደሚወጡት የሚና ገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሁኔታው ጊዜ ከወሰደ በሁዋላ በባሎቻቸው ዘንድ መታወቁም ባይቀር እንኩዋን ለልጆቹ ሊደረግላቸው ክትትልና ጥንቃቄ እንዲሁም እንክብንቤ ላይ ተጽእኖ ስለሚያደርግ ይህ መስተካከል የሚገባው ክፍተት ነው፡፡ ..

በሐረር ጠቅላላ ሆስፒል ዙሪያ ካሉት አምስት ሳተላይት ክሊኒኮች የአንዱ ማለትም የአዋሽ ክሊኒክ ባለቤት ዶ/ር ኮከብ መሐመድ የሳተላይት ክሊኒኮቹን የስራ ባህርይ እንደሚ ከተለው ገልጸዋል፡፡

..... የሃረር ጠቅላላ ሆስፒታል የተቋቋመው በሐረር ከተማ ውስጥ ባሉ የጤና ባለሙያዎች አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ ሆስፒታል ውስጥ አምስት የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች የሚሰሩ ሲሆን እነዚህ ሐኪሞች በግላቸው ሌላ ክሊኒክ ያላቸው ናቸው፡፡ነገር ግን በጋራ ያቋቋምነውን ይህንን ሆስፒታል ማእከል በማድረግ በየክሊኒካችን የሚስተ ናገዱ ታካሚዎችን ከፍ ላለ ሕክምና ወደዚህ ሆስፒታል የምናስተላልፍ ሲሆን እኛ ሐኪሞቹም በዚህ ሆስፒታል እንደየአስፈላጊነቱ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡ በተለይም ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በሚሰጥ የስልጠናና ሌሎች ድጋፎች በተጨማሪ መንግስት አስፈላጊውን አቅርቦት ስለሚያደርግልን በተሻለ ሁኔታ ህብረተሰቡን ለማገልገል ችለናል፡፡ የጤና አገልግሎት ሽፋን በተናጠል ሊሰራ የሚችል አይደለም፡፡ መንግስትም ሆነ የግል የህክምና ተቋማት ለየብቻቸው እንስራ ቢሉ ውጤታማ ሊሆኑ እንደማይችሉ እሙን ነው፡፡ ስለዚህም ተቀናጅተን መስራት በመቻላችን የሰዎችን ሕክምና ለማግኘት ከቦታ ቦታ መዘዋወር ቀንሰናል ብለን እናምናለን፡፡ የመካንነት፣የማህጸን ካንሰር ፣ከፍተኛ የራጅ ምርመራ ለመሳሰሉት ሁሉ ወደአዲስ አበባ የሚኬድበትን የመንገድ የሆል የመሳሰ ሉትን ወጪዎች ከመቀነስ ባሻገርም አገልግሎቱ ተጠቃሚዎቹ ባሉበት በአካባቢያቸው በመድረሱ ጊዜ ሳይፈጅ በፍጥነት ሕክምናን ማግኘት አስችሎል፡፡ ስለዚህም የኤችአይቪ ታካሚዎች እንደቀድሞው አድሎና መገለል የሚባል ነገር ሳይደርስባቸው እንደማንኛውም ታካሚ በቅርባቸው በሚያገኙት የህክምና ተቋም በመገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ብዙዎችን መድረስ ችለናል ብለን እናምናለን፡፡..

በስተመጨረሻም የሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር እና የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አየለ ኃይሉ በተለይም ሕጻናቱ በኤችአይቪ ቫይረስ እንዳ ይያዙ በማስቻሉ ረገድ ያላቸውን እማኝነት ገልጸዋል፡፡

.....ኤችአይቪን በተመለከተ የባህርይ ለውጥ ለማምጣት ገና ህብረተሰቡን ማስተማር መቀጠል አለበት፡፡ አሁንም ገና ነው፡፡ እርጉዝ የሆኑትን በመንከባከብና ሕጻናቱ ከቫይረሱ ጋር እንዳይወለዱ ለማድረግ ግን ተገቢውን ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ሀምሳ አራት እናቶች ከተወለዱ ሕጻናት መካከል ሁለቱ ሕጻናት ብቻ ናቸው ቫይረሱ የተገኘባቸው፡፡ ይህንን ስሌት ወደመቶ ብንቀይረው 97 ያህል ሕጻናቱን አድነናል ማለት ነው፡፡ ይህ ትልቅ እርካታ ነው፡፡ የዚህም ምክንያቱ እናቶች አስቀድሞ ውንም ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ ተገቢውን ምክር እየለገስናቸው ስለሆነ እና እነሱም ተቀብለው ተግባራዊ በማድረጋቸው የተገኘ ውጤት ነው፡፡ስለዚህ ሐገሪቱን የሚረከቡዋት ሕጻናት በጤንነት በመወለድ ላይ ናቸው ማለት እንችላለን፡፡ የባህርይ ለውጥ ለማምጣት ግን ገና ብዙ ስራ መሰራት አለበት፡፡ ..

 

 

Read 1764 times Last modified on Friday, 13 July 2012 16:24