Saturday, 20 June 2020 12:00

“ጣና ሀይቅ የሀገር ሀቅ” ጉዞ ትላንት ተጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ጉዞው አርቲስቶቹን ግሩም ኤርሚያስ፣ ደሳለኝ ሀይሉ፣ ሽመልስ አበራ፣ ዳንኤል ተገኝና አክቲቪስት ኦባንግ ሜቶን ሌሎችን ያካትታል

             ጣና ሀይቅ በመጤው አረም “እምቦጭ” ከተወረረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ የደረሰበትን ጉዳት የሚያስገነዝብና ለሀይቁ የሚመለከተው ሁሉ ትኩረት እንዲሰጥ ለማሳሰብ ያለመ “ጣና ሀይቅ የሀገር ሀቅ” የተሰኘ የሚዲያና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ የጣና ጉዞ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በጉዞው ላይ አርቲስቶቹ ግሩም ኤርሚያስ፣ ደሳለኝ ሀይሉ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ ሽመልስ አበራና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ተካትተውበታል ይሆናል ተብሏል።
በዳጉ ኮሙኒኬሽን አማካኝነት በተዘጋጀው በዚህ ጉዞ፤ በዛሬው ዕለት በአዲስ ዘመን በኩል ባለው የጣና ክፍል የእምቦጭ ነቀላ የሚከናወን ሲሆን፤ ስለ ሀይቁ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት የሚተላለፍ እንደተካተቱበት ታውቋል፡፡  
በወደፊቱ የሀይቁ እጣ ፈንታ ላይም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል። ከዚሁ ጎን ለጎን፤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ሥርጭት ለመቀነስ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችም እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል።  

Read 11251 times